ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ወ/ሮ ሙሉነሽ ጉሌ ሱላ፣ ከአባቴ ከአቶ ጉሌ ሱላ ካልሳ እና ከእናቴ ከወ/ሮ ቀለሟወርቅ ዱልጌ በ1978 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ ዛላ ወረዳ፣ ዑባ ሻቻ ቀበሌ ተወለድኩ። የትምህርት እድሜዬ ሲደርስ፣ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ በዑባ ሻቻ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በጌልጣ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርቴን በሳውላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትዬ በ1994 ዓ.ም. አጠናቀቅሁ። በ1997 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዙር የጤና ኤክስቴንሽን ሥልጠናዬን ካጠናቀቅሁ በኋላ፣ በወቅቱ በጋሞ ጎፋ ዞን፣ ዛላ ወረዳ፣ በራ ውይጋ ቀበሌ ተመድቤ ለ6 ተከታታይ ዓመታት በጤና ሙያ ዘርፍ አገለገልሁ። ከዚህ በመቀጠል፣ የትምህርት እድል በማግኘት ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም. ለሁለት ዓመታት በአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመማር በዲፕሎማ ተመረቅሁ። የዲፕሎማ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ በዛላ ወረዳ ከጽ/ቤት ኃላፊነት ጀምሮ እስከ ወረዳ አስተባባሪነት ድረስ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ለ6 ተከታታይ ዓመታት አገለገልሁ።ከዚህ የሥራ ልምድ በኋላ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት እድል በማግኘት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በህብረተሰብ ጤና (HO) ትምህርት ተከታትዬ ተመረቅሁ።ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2019 ዓ.ም. ድረስ በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ/ኢ/ስ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገለግያለሁ። በዚህ የሥራ ዘመን የተሰጠኝን ኃላፊነት በትጋት፣ በተጠያቂነትና በታማኝነት ለመወጣት ጥረት አድርጌያለሁ። በግል ሕይወቴ ባለትዳር ስሆን፣ የሦስት ልጆች እናት ነኝ። በተጨማሪም የሦስት ልጆች አሳዳጊ በመሆን የቤተሰብ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ እገኛለሁ።