ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
6
ክልል:
አዲስ አበባ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
እኔ አቶ ሳምሶን ወንድሜነህ እሸቴ ከእናቴ ወ/ሮ ጀሚላ ሁሴን አባጋሮ ከአባቴ አቶ ወንድሜነህ እሸቴ አደፍርስ በመጋቢት 19/1976ዓ.ም በቀድሞ ዞን 6 ቀበሌ 05 ልዩ ስ ፉኛን ዳራ በተሰኝ ልዩ መንደር ውስጥ የተወለድኩ ሲሆን እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ እንደሁሉም ኢትዮጲያዊ የቄስ ትምህርት በመግባት ፊደል መቁጠር የጀመርኩ ቢሆንም ድንገት በደረሰብኝ አደጋ የአይን ብርሀኔን ማጣቴ ቤተሰቦቼን ጓደኞቼን እና የመንደሯ ነዋሪ እጅግ ከማስደንገጡም በላይ በተለይም የናቴን ልብ ሰበረ ሆኗል ፡፡ እናቴና ጥቂት ልበ ቀና የአካባቢው ነዋሪዎች የአይን ብርሀኔ እንዲመለስ በጠበል በዱአና በፀሎት ከመሞከራቸውም ባሻገር በዘመናዊ ህክምና እጅግ ብዙ ቢዳክሩም መፍትሄ ባለመገኘቱ የአይነስውራን አዳሪ ት/ቤት ገብቼ ትምህርቴን እንድከታተል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልኝ 1987-1990 እስከ 6ኛ ክፍል ምራብ ሸዋ ባኮ ትቤ ወረዳ ባኮ ከተማ ላይ በሚገኘው የአይነስውራን ት/ቤት 1991-1992 በአቃቂ ፊትአውራሪ አባይነህ መተኪያ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 7እና8ኛ ክፍልን በ1993 በቀድሞ አቃቂ ከፍተኛና አጠቃላይ ት/ቤት 9ኛ ክፍልን 1994 እስከ 1996 በደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ት/ቤት 10አእስከ12ኛ ክፍል የቀለም ትምህርቴን ተምሬ በማጠናቀቅ ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ተፈትኜ ወደ ዩንቨርሰቲ ለመግባ የሚያስችለኝን ውጤት በማስመዝገቤ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲን ተቀላቅዬ ከ1997 እስከ 1999የታሪክ ትምህርቴን በመከታተል የተመረኩ ሲሆን የትምህርት ሚኒስተር ያወጣውን የስራ ማስታወቂ ተወዳድሬ በማለፍ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አማካኝነት ደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ት/ቤት ተመድቤ ለ1 አመት ተመድቤ በመምህርነት ያገለገልኩ ሲሆን ከ2001 እስከ 2002 በበሰቃ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት ከ2003 እስከ 2004 በአቃቂ ወረዳ 01 ት/ፅ/ቤት በሀላፊነት ከ2004 ግማሽ እስከ 2005 ግማሽ በአቃቂ መንግስት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት ከ2006 እስከ 2007ዓ.ም በአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት በተጨማሪም ከ2008 እስከ 2012 በዚሁ ት/ቤት በዋና ር/መምህርነት 2013 እስከ 2014 በደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ት/ቤት በዋና ር/መምህርነት 2015 እስከ አሁን ድረስ በአዲስ አበባ ማረሚያ አንደኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በዋና ር/ መምህርነት ከማገልገሌም በላይ በአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር አቃቂ ቅርንጫ ፅ/ቤት በወጣቶች ማህበር በዱና ፀረኤርሰስ በአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ከአባልነት እስከ አመራርነት በመሳተፍ በተለያዩ የበጎ ስራዎች ውስጥ የበኩሌን ሚና በማበርከት የኢኮኖሚ አቅም ችግር ያለባቸው ሰዎች የትምህርት ግብአት ህክምና የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው በማገዝ አርያነት የተላበሰ ተግባራትን በማከናወን በቀድሞ የኢሀዲግ ፓርቲ በዴህድን አደረጃጀት በንቃት በመሳተፍና እራሴን በማሳየት በፖለቲከ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው መታገል ከመቻሌም በላይ ከ2010ጀምሮ ከለውጡ ወዲህ የፖለቲካ እንቅስቃሴው ሰው ሰው የሚሸት ወንድማማችነትን የሚበረታታ ሁለንተናዊ ተሳትፎን የሚጋብዝ በመሆኑ በአባልነት በመቀጠሌ እና ከፍ ያለ ተሳትፎ በማድረጌ በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ፓርቲዬ ብልፅግና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አወዳድሮኝ 5 አመቱን በአባልነት በመሰረተልማትና ትራንስፖርት እንዲሁም በሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ ጉልህ አበርክቶት የነበረኝ ሲሆን በድጋሚ ፓርቲዬ የነበረኝን አስተዎፆ በማየት በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓርቲዬ አዲስ አበባ ን እንድወክል አቅርቦ ያወዳደረኝ ሲሆን ፓርላማው በአዲስ መልክ ከተመሰረተ በኋላ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እራሴን አዘጋጅቻለሁ በየጊዜው እራሴን ለማሻሻል የመጀመሪያ ድግሪ ከተማርኩ በኋላ ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ፒጂዲሴል ከኮተቤሜትሮፖሊያን ዩንቨርስቲ ኢዲኤልኤም ኢድኬሽናል ሊደር ሺፕ ማኔጅመንት በሁለተኛ ድግሪ የተመረኩ ከመሆኑም በላይ በመራኋቸው ተቋማት ሞዴል ተቋም በመፍጠር እና ተማሪዎችን ውጤታማ በማድረግ እንዲሁም በጎ ስራዎች ማህበራዊ ተሳትፎ አራአያነት ያላቸው ተግባራትን በማከናወን ተቋማቱን እና እራሴን ለሽልማት ማብቃት ከመቻሌም በላይ በአሁኑ ወቅት ትዳር በመያዝና ቤተሰብ በመመስረት የ4 ቆነጃጅት ሴት ልጆች አባት ከመሆኔም በላይ የራሴን ወንድሞች የባለቤቴን እህቶች ከልጆቼ ጋር አብሬ በማኖርና ለወግ በማብቃት የምርጥ አባታዊ ሚናዬን ለመወጣት ችያለሁ ፡፡