ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የሕይወት ታሪክ
የግል መረጃ
ሙሉ ስም፡ ወ/ሮ ቤተልሔም ጉሌ ተስፋው
ዕድሜ፡ 36 ዓመት
የትውልድ ቦታ፡ የሳስምባ ወረዳ፣ መርሃቤቴ ቀበሌ፣ ደንጋባ
የትውልድ ዘመን፡ 1982 ዓ.ም.
የትምህርት ዝግጅት
ወ/ሮ ቤተልሔም ጉሌ ተስፋው በትምህርት ዕድሜያቸው ሲደርስ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በየሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በዘይታ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል በአርበኞች 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በመሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
በ2004 ዓ.ም. የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በማምጣት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም. በመማር በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በተጨማሪም ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ብርሃን ኮሌጅ በመማር በቪዠዝነስ ማኔጅመንት ትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ (MBA) አጠናቀዋል።
የሥራ ልምድ
ወ/ሮ ቤተልሔም ጉሌ ተስፋው ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም. በገንዘብ ጽ/ቤት በባለሙያነት ለአራት ዓመታት አገልግለዋል።
ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም. በገንዘብ ጽ/ቤት የጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪ በመሆን ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።
ከ2015 እስከ ጥቅምት 2018 ዓ.ም. በመርሃቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።
ከህዳር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በመርሃቤቴ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
የማኅበራዊና የአገልግሎት ተሳትፎ
ወ/ሮ ቤተልሔም ጉሌ በሥራ ዘመናቸው ባካበቱት የአመራር፣ የአስተዳደርና የማኔጅመንት ልምድ በገጠርና በከተማ ማኅበረሰብ ዘንድ ተደማጭነትና ተወዳጅነት ያተረፉ ታማኝ፣ ቅንና ትጉህ አገልጋይ ናቸው።
በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ውስጥ በመሳተፍ ለማኅበረሰቡና ለሕዝብ አገልግሎት ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል።
የአሁኑ ኃላፊነት
በአሁኑ ወቅት ወ/ሮ ቤተልሔም ጉሌ ተስፋው የመርሃቤቴ ወረዳ አለም ከተማ ምርጫ ክልልን ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል።
በዚህም ኃላፊነት የሕዝብን ጥቅም በማስቀደም፣ የማኅበረሰቡን ድምፅ በማሰማትና ለሀገራዊ ልማት አስተዋጽኦ ለማድረግ በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።