የሕይወት ታሪክ

ወ/ሮ  አስቴር ዳዊት ጦሼ ከአባታቸው ከቢሾፕ ዳዊት ጦሼ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ እሞቴ ዋዲሶ በወላይታ ሶዶ ከተማ ነሃሴ 30/1974 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛሉ።  የሥራ ልምዳቸውን በአጭሩ ለመግለፅ ያህል በስትራቴጂካዊ አመራርነት ለ18 ዓመታት እና በባለሙያነት አገልግሎት 2 ዓመትን ጨምሮ ላለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የመንግሰትና የፓርቲ ኃላፊነቶች ላይ ያገለግሉ ሲሆን ከእነዚህም ወስጥ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ እና የቱሪዝም ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በቀድሞ የብ/ብ/ህ/ክ መንግስት እና በወላይታ ዞን በተለያዩ የአመራር እርከኖች ተሿሚ ሆነው አገልግለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የ5ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን ለ7ኛ ዙር በተካሄደው ምርጫ ሶዶ ዙሪያን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኖ ተመርጠዋል። ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ባለትዳር እና የ4 ልጆች እናት ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (B.Sc.) ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን (M.Sc.) ደግሞ በሥራ አመራር (Management) ከኔዘርላንድ ስቫንሃል ላረንስታይን (Van Hall Larenstein) ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።  5 ቋንቋዎችን የሚናገሩ ተግባቢ ሲሆኑ በትርፍ ጊዜያቸው መጽሐፍትን ማንበብ፣ በማህበረሰብ ልማት፣ በበጎ አድራጎት እና በከተማ ግብርና (አረንጓዴ ልማት) እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት ይሳተፋሉ።