የሕይወት ታሪክ

መስፍን እሮካቤ እባላለሁ የተወለድኩት ጎንደር አዘዞ ከተማ መጋቢት 20/1955 ዓ.ም ነዉ ። እድሜ ለትምህርት እንደደረሰ የመጀመሪያ ደረጃ በአፄ ፋሲል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሬ አለሁ ፤7ኛ ና 8 ኛ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተምሬ አለሁ ። በአዘዞ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በአዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቄ አለሁ ። ሀገሬን በዉትድርና ለማገልገል ኮማንዶ ወታደር ሰልጥኘ በምስራቅ በኦጋዴን ና በሰሜን በኤርትራ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተዋግቻለሁ በዚህ ዉጊያ ሶስት ጊዜ በስድስት ጥይት ቆስያለሁ ። በመጨረሻም በደረሰብኝ አካል ጉዳት በሀኪሞች ዉሳኔ ከሰራዊቱ በቦርድ ተሰናብቻለሁ ።በመቀጠል መምህራን ኮሌጅ ገብቸ በማህበራዊ ሰይንስ ተመርቄ መምህር፣ ርእሰ መምህር፣ሱ ፐርቫይዘር ና የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሁኘ አገልግያለሁ ።በተመሳሳይ በጎንደር ዩንቨርስቲ በህግ ድግሪ ፤በሰባዊ መብት ደግሞ ሁለተኛ ድግሪ ተመርቄ አለሁ በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህግና የልማት የሰላም አማካሪ ሁኘ አገልግያለሁ ። በአጠቃላይ የምወዳትን ለገሬን ላለፉት 46 ዓመታት በ8 ሴክተር መስሪያ ቤት በቅንነት በታማኝነት በጀግ ንነት በአርበኝነት አገልግያለሁ ። በአገለገልኩባቸዉም ተቋማት በኮኮብ ሰራተኛነት ተሸልሜ አለሁ ።