የሕይወት ታሪክ

እኔ ኤሚሊ ሀመዱ አሊ እባላለሁ፤ የተወለድኩት በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ በ1987 ዓ.ም ነው። በቤተሰቤ ውስጥ ብቸኛ ሴት ልጅ በመሆኔ በከፍተኛ እንክብካቤ እና ፍቅር ያደግኩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ባለትዳርና የ7 ልጆች እናት ነኝ። ገና በወጣትነቴ ለህዝብ አገልግሎት እና ለለውጥ ትልቅ ፍላጎት ነበረኝ። የትምህርት እና የዕውቀት ጉዞዬ መሰረታዊ ትምህርት (ከ1ኛ - 10ኛ ክፍል)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ኮሙኒቲ ትምህርት ቤት ተከታተልኩ። ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ (ከ10ኛ - 12ኛ ክፍል)፦ በአፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ በሚገኘው ነመሌፋን መሰናዶ ትምህርት ቤት አጠናቀቅኩ። የከፍተኛ ትምህርት፦ በ2006 ዓ.ም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሀብት (Natural Resources) የባችለር ዲግሪዬን ተቀበልኩ። የፖለቲካ እና የህዝብ አገልግሎት ጉዞዬ በትምህርት ገበታዬ ያገኘሁትን እውቀት ከአካባቢዬ ህዝብ ፍላጎት ጋር በማቀናጀት በለጋ እድሜዬ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተቀላቀልኩ።በ5ኛው የምርጫ ወቅት (ከ2008 - 2012 ዓ.ም) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆጜ የሰራሁ ሲሆን፣ በዚህም ጊዜ በቋሚ ኮሚቴ ደረጃ በህዝብ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ መብቶች እና ልማቶች ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርጌአለሁ። ለፓርላማ አባልነት በበቃሁበት ወቅት (በፈረንጆች አቆጣጠር 2019) የወጣቶች እና የሴቶችን ድምፅ በከፍተኛ ደረጃ በማሰማት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የራሴን አሻራ ማሳረፍ ችያለሁ። የትዳርና የቤተሰብ ሀላፊነቴን (የ7 ልጆች እናትነቴን) ከመንግስትና ህዝባዊ ሀላፊነቴ ጋር አጣጥሜ በመምራት፣ እንዲሁም በወጣትነት እድሜዬ በከፍተኛ የሀገር ሀላፊነት ደረጃ ላይ በመድረሴ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና እናቶች አርአያ ለመሆን ጥሬአለሁ።