ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የግል ሕይወት ታሪክ ፦ ኢሳ ሀሰን ሙሀመድ
1. መግቢያና የትውልድ ዘመን
እኔ ኢሳ ሀሰን ሙሀመድ በባሌ ዞን፣ አጋርፋ ወረደ፣ አማለማ ቀበሌ ነሐሴ 12 ቀን 1977 ዓ.ም. ተወለድኩ። ያደግኩት ከአባቴ አቶ ሀሰን ሙሀመድ እና ከእናቴ ወ/ሮ መዲና ሳዶ አርሶ አደር ቤተሰብ ነው። ቤተሰቦቼ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ እውነተኛነትን እና ትህትናን የሚያስቀድሙ፣ የኦሮሞን መልካም ባህልና የእስልምና እምነት እሴቶችን በጥብቅ የሚከተሉ ነበሩ።
የልጅነት ጊዜዬ ከትምህርት ጎን ለጎን የቤተሰብን በጎች በመጠበቅ እና እናቴን በቤት ውስጥ በማገዝ፣ የታዛዥነትና የጠንካራ ሥራ ባህልን በመቅሰም ያለፈ ነበር።
2. የትምህርትና የእድገት ዘመን
• የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በወይብ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ደግሞ በአጋርፋ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ። በትምህርት ዘመኔ በተለይም የሕሳብ እና የታሪክ ትምህርቶችን አብልጬ እወድ ነበር።
• የከፍተኛ ትምህርት፦ የመጀመሪያ ዲግሪዬን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር (History and Heritage Management) የተከታተልኩ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪዬን (M.A.) ደግሞ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሶስዮሎጂ (Sociology) ትምህርት መስክ በከፍተኛ ውጤት አጠናቅቄአለሁ።
• ልዩ ክህሎትና ተሰጥኦ፦ ገና በተማሪነት ዘመኔ የአመራር ክህሎቴን በማሳየት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆኜ አገልግያለሁ። በተጨማሪም በስፖርት ዘርፍ በቮሊቦል (Volleyball) ተጫዋችነቴ እታወቅ ነበር።
3. የሥራ፣ የአመራርና የሙያ ጉዞ
የሙያ ሕይወቴን በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በረዳት መምህርነት (Graduate Assistant) የጀመርኩ ሲሆን፣ የትምህርት ደረጀዬን በማሳደግ ረዳት ፕሮፌሰርነት ላይ ደርሻለሁ። በሂደት በከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ በመመደብ ተቋማዊ ለውጦችን ለማምጣት ሰርቻለሁ፦
• የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ (መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ)፦ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሙን በማስፋፋት በርካታ አዳዲስ የድህረ ምረቃ ትምህርት መስኮች (Postgraduate Programs) እንዲከፈቱ የማስቀንጠሪያ ሚና ተጫውቻለሁ።
• የተማሪዎች አገልግሎት ዲን፦ የተማሪዎችን የምግብ፣ የመኝታ፣ የክሊኒክ እና የመዝናኛ ስፍራዎችን ጥራት ለማሻሻል ሰፊ የተቋም ሪፎርም አድርጌአለሁ።
• የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ዘርፍን በሕግና አሠራር ደንብ ላይ በመመሥረት ተቋሙ መዋቅራዊ እድገትና ለውጥ እንዲያመጣ እየመረው እገኛለሁ።
• ያጋጠመ ፈተናና ጽናት፦
በተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍ አጠቃላይ ሪፎርም በማካሄድ ላይ ሳለሁ፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ጥቂት ሠራተኞች በተደራጀ መንገድ ተቃውሞ በማንሳት እስከ ዩኒቨርሲቲው ቦርድ ድረስ ክስ መስርተውብኝ ነበር። ነገር ግን ለሕግና ለሙያ ሥነ-ምግባር በመቆም፣ በአቋሜና በእውነተኝነቴ በመፅናት ሂደቱን በአሸናፊነት አልፌዋለሁ።
4. ማኅበራዊና ቤተሰባዊ ሕይወት
• ቤተሰብ፦ ባለትዳርና የ4 ሴቶች እና የ3 ወንዶች (በጠቅላላው የ7 ልጅ) አባት ነኝ። በሙያና በአመራር ጉዞዬ ውስጥ ከቤተሰቤ ከፍተኛ ድጋፍና እገዛ ይደረግልኛል።
• ማኅበራዊ ተሳትፎና መዝናኛ፦ በማህበረሰብ አገልግሎትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ አለኝ። በትርፍ ጊዜዬ መጻሕፍትን ማንባብ፣ ስፖርት መስራት እና የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት ያስደስተኛል።
5. የሕይወት መርህና መደምደሚያ
በሕይወቴ የምመራባቸውና የማልደራደርባቸው ዋና ዋና እሴቶች ታማኝነት፣ ቅን አገልግሎት፣ በእውነት ላይ መፅናት እና አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን በድፍረት መወሰን ናቸው።
እስከ ዛሬ ባሳለፍኩት የትምህርት፣ የሥራና የአመራር ጉዞ የተረዳሁት ትልቁ ነገር፣ የሰው ልጅ በእውነትና በሕግ ላይ ጸንቶ ከሰራ ማናቸውንም መሰናክሎች አልፎ ለተቋምም ሆነ ለማህበረሰብ የሚጠቅም ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ነው።