የሕይወት ታሪክ

በቦረና አውራጃ በደብረሲና ወረዳ በ063 ደራሚ ቀበሌ በላፍቶሎላ መንደር ከአባቴ ከአቶ ወድ ይመር ተሰማ እና ከእናቴ ከወ/ሮ ደብርነሽ አበጀ ካሳ መሰከረም 12/1964 ዓ.ም ተወለድኩኝ እድሜዬ ለትምህርት እንደደረስኩ በ1975-1978 ዓ.ም ከ1ኛ አሰከ 4ኛ ክፍል በሶዬ ፩ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት በ1979 ዓ.ም ፭ኛ ክፍል ደንሳ ከራባ ፩ኛ ጀረጃ ትምህርት ቤት በ1980 ዓ.ም ፮ኛ ክፍል በለገ አማራ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1981 ዓ.ም ፯ኛ ክፍል በቦረና ፩ኛ እና መለስተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤት የተማርኩኝ ሲሆን በጥቅምት 12/1982 ዓ.ም ወደ ትጥቅ ትግል በመግባት ከደርግ ድምሰሳ እስከ ሀገራዊ የሽግግር መንግስት ምስረታ በአማራ፣በአድስ አበባ፣በኦሮማያ፣በደቡብ፣በሐረር፣በአፍር እና በሱማሌ ልዩ ልዩ የሀገሪቱ uክፍሎች ከተራ ወታደር እስከ ሻለቃ አዛዥነት የመራሁ ሲሆን በ1984 ዓ.ም ለምሕንድስና ትምህርት ከሐረር ኦጋዴን አካባቢ ከጦር ክፍሌ ተመልምዬ በኢትዩጵያ የሽግግር መንግስት የአገር መከላከያ ሚኒስቴር መሐንድስ እዝ በኮንስትራክሽን መሃንድስ በአድስ አበባ ምሕንድስና ትምህርት ቤት ተምሬ በሰርተፊኬት ተመርቄ በምስራቅ እዝ መሀንዲስ መምሪያ በ1985 ዓ.ም ትዳር መስርቼ ሳገለግል የቆየሁ ሲሆን በነበረኝ ውጤታማ ስራ የበ1987 ዓ.ም በሐረር ኮር ስታፍ ት/ቤት የ8ኛ ክፍል የመማር እድል በማግኘት የተሻለ ውጤት በማምጣት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በአድስ አበባ ግንቦት 20 ትምህርት ቤት እንድማር በመከላከያ በኩል እድሉን አገኝቼ እስከ በ1989 ዓ.ም የ1 ወንድ ልጅ አባትና 11ኛ ክፍል የተማርኩ ሲሆን በ1990 ዓ.ም ሀገራችን ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ትምህርቱን በማቋረጥ ጦር ሰራዊት እየመራሁ ሀገሬን ከወረራ ለመታደግ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የገባሁ ሲሆን በዚሁ ጦርነት በተለያዩ አውድ ውጊያዎች በተለያየ ግንባር ጦርነት ውስጥ በተደጋጋሚ አኩሪ የጀግንነት ድሎችን በመቀዳጀት የጦር ሜዳልያ የተሸለምኩ ሲሆን በዚሁ ጦርነትም በተደጋጋሚ በመቁሰል በ1993 ዓ.ም የ1 ሴት ልጅ አባት በመሆን ከመከላከያ በክብር በመሰናበት ወደ ትውልድ ቦታየ በመመለስ የ12ኛ ክፍል ትምህር በማጠናቀቅ የዲፕሎማ እና የመጀመሪያ ድግሪ በአስተዳደር አመራር በመማር በነበረኝ የስራ አፈፃፀም የ2ኛ ድግሪ በሕግ ትምህርት እድሉን አግኝቼ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የተማርኩ ሲሆን በመንግስት ስራ የመከነ ሠላም ከተማ ቀበሌ ሊቀመንበር፣የመከነ ሰላም ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅ ፣የቦረና ወረዳ አስተዳደር ፀጥታ ኃላፊ ፣የቦረና ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ኃላፊ፣ የቦረና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ፣የቦረና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ፣የደሴ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የፋትህ መምሪያ ኃላፊ እና የከንቲባ ኮሚቴ በመሆን እያገለገልኩ ሲሆን አሁን ደግሞ በአጠቃላይ የ3 ወንድ ልጆች እና የ4 ሴት ልጆች በድምሩ የ7 ልጆች አባት ስሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግናን በመወከል በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የምርጫ ክልል ደብረሲና ቁጥር 1 ለተወካዮች ምክርቤት በእጩነት በመቅረብ እና በመወዳደር ከፋተኛየሕዝብ ድምጽ በማምጣት ለፓርላማ ውክልና ወስጃለሁ።