ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ጎርቼ
ክልል:
ሲዳማ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ደምሴ ስኳሬ ሳኩማ የህይወት ታሪክ:-
ስሜ ደምሴ ስኳሬ ሳኩማ እባላለሁ፤ የ40 ዓመት ዕድሜ ጎልማሳ ፖለቲከኛ ስሆን፣ በ2018 ዓ.ም. ለ7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ከሲዳማ ክልል ጎርቼ የምርጫ ክልል የተመረጥኩ የፓርላማ አባል ነኝ።
ውልደቴ በኢትዮጵያ፣ ሀዋሳ ከተማ በሰኔ 14 ቀን /1979 ዓ.ም. ከአባቴ ስኳሬ ሳኩማ እና ከእናቴ ትዕግስት ዋንሳራ ኩሞ ተወለድኩ። ሲዳምኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛን አቀላጥፌ እናገራለሁ። ዝንባሌ እውነትን፣ የሕዝብን ጥቅም፣ ሰላማዊ አብሮ መኖርን፣ ገንቢ ውይይትን እና ኃላፊነት ያለውን አገልግሎት አስቀድማለሁ።
እኔ በሙያዬ ኢኮኖሚስት፣ የልማት ባለሙያ፣ የቢዝነስ ሥራ አስኪያጅ እና ልምድ ያለኝ የድርጅት መሪ ነኝ። በኢኮኖሚክስ፣ በፋይናንስ አስተዳደር፣ በፕሮጀክት ዕቅድ ዝግጅት፣ በህብረት ሥራ ልማት፣ በገበያ ማስፋፊያ፣ በሎጂስቲክስ እና በድርጅት አስተዳደር ጠንካራ የሙያ ዕውቀት አለኝ።
የሙያ ልምዴ በሕዝብ አስተዳደር፣ በልማት ድርጅቶች ሠራተኛ፣ በኢንሹራንስ ኩባኒያ መሪ፣ በግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ማማከር፣ በግል የንግድ ዘርፍ እና በማምረቻ ዘርፍ የተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶችን ያካትታል።
ልምዴ የሚያጠነጥነው በዕቅድ ዝግጅት፣ በአስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም፣ በሰው ኃይል አስተዳደር፣ በቢዝነስ ልማት ሥራ፣ በክትትልና ግምገማ፣ በግዥ፣ በሎጂስቲክስ እና በድርጅታዊ ውሳኔ አሰጣጥ ዘርፎች በተራማጅነት የተጠናከረ ኃላፊነትን መወጣቴን ያሳያል።
የትምህርት እና የአካዳሚክ ዝግጅት፡-
በኢኮኖሚክስ፣ በልማት ኢኮኖሚክስ እና በቢዝነስ አስተዳደር ጠንካራ የአካዳሚክ መሠረት አለኝ።
በ2014 ዓ.ም. ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የልማት ኢኮኖሚክስ ማስተር ዲግሪ (MA in Development Economics) አግኝቻለሁ። በትምህርቴም የልማት ኢኮኖሚክስ፣ ማይክሮና ማክሮ ኢኮኖሚክስ፣ እንዲሁም የፕሮጀክት ዕቅድና ትንተናን ትኩረት ሰጥቼ አጥንቼአለሁ። በምርምር ሥራዬም ከፍተኛ ውጤት አግኝቼአለሁ( በጣም ጥሩ)፡፡
ከዚያ አስቀድሞ በ2001 ዓ.ም. በተመሳሳይነት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA in Economics) አጠናቅቄያለሁ። በዚህም ጥናት የኢኮኖሚክስ፣ የማኔጅመንት እና የሒሳብ አያያዝ መርሆችን ተምሬያለሁ። በተጨማሪነትም ጎን ለጎን በ2012 ዓ.ም. በInternational Institution of Church Management in Florida (IICM) በተባበረ ተቋም በኩል የቢዝነስ አስተዳደር ማስተር ዲግሪ (MBA) አግኝቻለሁ።
በዚህ የትምህርት ዘርፍ የሒሳብ አያያዝ፣ የፋይናንስ አስተዳደር፣ የጊዜ አጠቃቀም አስተዳደር፣ የኮሌጅ አስተዳደር እና ተዛማጅ የአስተዳደር ሥራዎችን አጥንቼአለሁ።
ተጨማሪ የሙያ ሥልጠናዎቼ የልማት ፕሮጀክቶችን ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣ በብቃት ላይ የተመሠረተ የኢንተርፕራይዝ ምሥረታ፣ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሲቪል ማህበረሰብ አቅም ግንባታ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የልማት ፖሊሲ ጋር ተያያዥ ሥልጠናዎችን ያካትታሉ።
የአመራር እና የሙያ ጥንካሬዎች፤-
የሥራ ልምዴ በፋይናንስ አስተዳደር፣ በበጀት ዝግጅት፣ በለጋሽ ተቋማት ገንዘብ አስተዳደር፣ በሒሳብና ሪፖርት ዝግጅት፣ በድርጅታዊ ዕቅድ፣ በፕሮጀክት አስተዳደር፣ በስትራቴጂክ አስተሳሰብ፣ በሰው ኃይል አስተዳደር፣ በግዥ፣ በሎጂስቲክስ፣ በክትትልና ግምገማ እና በቢዝነስ ልማት ጠንካራ ብቃት እንዳለኝ ልምዶቼ ያሳያል። ባልደረቦቼ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ የማበረታታ፣ ገንቢ አስተያየትና ትችትን የማከብር እና የሥራ ቦታ ግጭቶችን በአዎንታዊ መንገድ የምፈታ ሰው ነኝ።
በተማርኩት ትምህርት መስክ በኢንፎሊንግ ዩንቨርሲት ኮሌጅ፣በዩኒክስታር ኮሌጅ፣በአትላስ ኮሌጅ፣እና በሌሎች ኮሌጆች በቀጥታና በትርፍ ጊዜያት የማስተማር ልምድ አለኝ፡፡
የሙያ ልምዴ በተጨማሪም በራሴ ተነሳሽነት መሥራት፣ የአሠራር ውሳኔዎችን መስጠት፣ የድርጅት ሀብቶችን ማስተዳደር፣ ቡድኖችን መምራት፣ የተግባር ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት፣ አፈጻጸምን መከታተል እና ለሚከሰቱ አዳዲስ ችግሮች በፍጥነት ምላሽ መስጠት እንደምችል ያሳያል።
ከሙያዊ ሥራዬ በተጨማሪ፣ በሲዳማ አርነት ንቅናቄ (SLM) የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እስከ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ድረስ የተለያዩ የአመራር ኃላፊነቶችን ተወጥቻለሁ። በተጨማሪም የሀዋሳ ከተማ የፓርቲ ጉዳዮች ኃላፊ እና በአስተዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ሆኜ አገልግያለሁ።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ የንግድና የገበያ ልማት ቢሮ የፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ሆኜ እየሠራሁ ነው። እንዲሁም የSLM አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የመድረክ ግንባር ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰብሳቢ ነኝ።
ቋንቋዎች እና ቤተሰብ
ሲዳምኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛን በማቀላጠፍ እናገራለሁ፤ በሦስቱም ቋንቋዎች መረዳት፣ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ እችላለሁ።
የአንዲት ቆንጆ ምስት ባል ስሆን፣ የሦስት ልጆች ማለትም የሁለት ሴት ልጆች እና የአንድ ወንድ ልጅ—አባት ነኝ። በተጨማሪም እናቴን እና ሁለት እህቶቼን፣ እንዲሁም ሁለት የቤት ሠራተኞችን በመደገፍና በመንከባከብ በአጠቃላይ የአስር ሰዎች ቤተሰብን እደግፋለሁ።
በመጨረሻም፣ የመረጡኝንም ሆነ ያልመረጡኝን ሕዝቦች ለመወከል እና በቻልኩት ሁሉ በፓርላማው ለማገልገል ራሴን በሙሉ ዝግጁ እያደረግሁ ነው።
ከአክብሮት ጋር!