ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የዶክተር ደበሌ ቃበታ ሁርሳ የህይወት ታሪክ
1. የትምህርት ሁኔታ
• ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ከፍተኛ ዲፕሎማ፤
• ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ፤
• ከኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት በተቋም አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪ፤
• ለንደን ከሚገኘው ግሪንዊች ዩኒቨርስቲ በትራንስፎርሜሽንናል ሊደርሺፕና የለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ
• በአሜሪካ ፍሎሪዳ ከሚገኘው ኪዌስት ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የዶክተሬት ዲግሪ (PhD) የትምህርት ደረጃ አላቸው።
2. የሥራ ሁኔታ
• በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የመንግሥት የአስተዳደር እርከኖች በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሰርተዋል፤
• በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ማስተባበርያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሰርተዋል፤
• ከ2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እየመሩ ይገኛሉ።
3. እውቅናና ሽልማት
• አራት ጊዜ የአፍሪካ የሥራ አመራር ምርጥ መሪ እውቅናና ሽልማት (The Best African Leadership Person of the Year) አግኝተዋል
• በሀገር ውስጥ የታክስ እና በጉምሩክ ሕግ ተገዥነት ላስመዘገቡት የቅንጅትና የላቀ አፈጻጸም ከ30 በላይ የእውቅና ሽልማቶችን አግኝተዋል።
4. ተጨማሪ የመንግሥታዊ አገልግሎቶች
• የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፤
• የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፤
• የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ አመራር ቦርድ አባል፤
• የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ተደራዳሪ ኮሚቴ አባል፤
• ብሔራዊ የኤክስፖርት ኮሚቴ አባል፤
• ብሔራዊ የታክስ ፎርስ አባል፤
• ሀገራዊ የኣምራች ካውንስል አባል እና በሌሎችም ኮሚቴዎች እያገለገሉ ይገኛሉ።