የሕይወት ታሪክ

ደጅይጥኑ አለነ ካአባቴ ከአቶ አለነ ዘውዴና ከእናቴ ከወ/ሮ ያቩን ጥላ ፀጋ በ1979 ዓ/ም በድባና ሰይፋጥራ ቀበሌ ተወለድሁ። እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስም በወሮታ ከተማ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተምሪያለሁ። ከዚያም የከፍተኛ ትምህርቴን ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ 2ኛ ዲግሪ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተምሪያለሁ። በመጄመሪያ ዲግሪ በደራ ወረዳ ፕሪፓራቶሪ መምህርነት አስተምሪያለሑ። በሁለተኛ ዲግሪዬ ደግሞ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና አስተማሪ በመሆን ሰርቻለሑ። ከ2014- አሁን ድረስ የፓርላማ አባል በመሆን እያገለገልሁ እገኛለሑ።