የሕይወት ታሪክ

እኔ አቶ ናኦል አባስ አብዲ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሸዋ ዞነ አዳአ በርጋ ወረዳ ስሬ በርጋ ቀበለ እቱ የምባል ልዩ ቦታ ወይም ዞን ከአቶ አበበ አብዲ በዳዳ እና ከወይዘሮ አበበች ኡርጋአ ዳዲ በጥር 12 ቀን 1978 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡ እንደ ማንኛዉም ገጠራማ ኢትዮጵያ ተወልዶ ያደጉ ልጆች ቤተሰቤን የተለያዩ ስራዎችን (ከብቶች በመጠበቅና የእርሻ ተግባራቶችን) በመስራት ወይም በማከናወን አድግለሁ። እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ በ1984 ዓ.ም ኢንጭኒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመግባት እዛዉ በ1991ዓ/ም 8ኛ ክፍልን ጨርሼ ወደ ሆለታ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቴን ተከታትያለሁ። በ1995 አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ/Addis Ababa Univarsity ተመድበ 1999 ከተፈጥሮ ሳይንስ ኮለጅ ከሂሳብ ትምህርት ክፍል በሂሳብ ትምህርት (Applied Mathematics/BSc) በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቄያለሁ። በዩኒቨርሲቲ ህይወቴ ውስጥ በ1996 በፖለቲካዊ ተጽእኖና በተለያዩ በሰላማዊ መንገዶች ባደረግኩት ትግል ምክንያት በአንድ ቀን ከትምህርታቸው ከተባረሩ ከ340 በላይ የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ዉስጥ አንዱ ነበርኩ። በ1999 ተመርቄ በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ በሚገኘው ባኮ ቲቤ ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር ሆኜ ሰርቻለሁ። ከ2002 እስከ 2008 ድረስ የኢንጭኒ ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ወይም ርዕሰ መምህር ሆኜ ህብረተሰበን አገልግያለሁ። ከ2009 እስከ 2010 የቡራዩ ከተማ እስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ እንድሁም ከ2011 እስከ 2013 የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የኦዲፒ/ብልጽና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆኜ አገልግያለሁ። ከ2015 እስከ 2018 ድረስ በሸገር ከተማ አስተዳደር የመልካ ኖኖ እና የቡራዩ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃም ወይም ምክትል አስተዳዳር እና የብልጽግና ፓርት ኃላፍ ሆኜ አገልግያለሁ። ከመደበኛ ሥራዬ ጎንለጎን የሁለተኛ ዲግሪዬን በተለያዩ መንገዶችየተለያዩ ትምህርት ዘርፎችን አጥንቻለሁ። ከአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ቤት አመራር (School Leadership) እና ከአክሞንልንክ ኮለጅ (Akmonlink Collage) በፕሮጀክት አስተዳደር (Project Management) ሁለተኛ ዲግዬን ጨርሻለሁ። ከባለቤቴ ወ/ሮ አቢዮት ጫላ ዋቃ ጋር በ2002 የተጋባን ስሆን በአሁኑ ሰዓት አንድ ወንድና አራት ሴት በአጠቃላይ አምስት ልጆች በጋራ ያፈራን ስሆን በአጠቃላይ ግን በአሁኑ ሰዓት ከእነና ከባልበቴ ጋር ስምንት የበተሰብ አባላትን በጋራ እያስተዳደርን እንገኛለን።