ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የትምህርት ዝግጅት
- የመጀመሪያ ድግሪዬን በታሪክ የወሰድኩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በታሪክ፣
- የማስተርስ ድግሪ በባዮሎጂካል/ፐሊየ አንትሮፖሎጂ ከቶኪዮ ዩኒቨርስቲ እና
- የማስተርስ ድግሪ በማህበራዊ/ሶሻል አንትሮፖሎጂ ከለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክሰ (LSE) አግኝቻለሁ፡፡
- የፒ.ኤች.ዲ (PhD) ድግሪዬን የወሰድኩት አሜሪካን አገር ከሚገኘው የዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርስቲ ነው፡፡
በመንግሥት የሥራ አገልግሎት
በመንግሥትና የሥራ ዓለም በሥራ ዓለም ከጀማሪ የጥናትና ምርምር ሠራተኝነት እስከ ከፍተኛ ሹመት ተመድቤ አገልግያለሁ፡፡
- የመጀመሪያ ድግሩዬን እንደተመረቅሁ ትግራይ ክፍለ ሐገር የባህል ሚኒስቴር የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጀማሪ ተመራማሪነት ተመድቤ ለሁለት ዓመታት አገልግያለሁ፡፡
- ከዚያም ወደ ሲዳሞ ክፍለ ሀገር ተዛውሬ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር የባህል ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ቡድን መሪ፣
- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት የባህልና ስፖርት ቢሮ ሲመሰረት በሹመት የባህል በምሪያ ኃላፊ፣
- ቀጥሎም በሹመት የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣
- የማስተርስ ትምህርቴን ጨርሼ ስመለስ የደ/ብ/ብ/ክ/መንግሥት የባህል፣ ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ በውደድር/ምደባ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
- ወደ 6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመርጬ ከመግባቴ በፊት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር መምህር እና
- የማህበራ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ የትምህርት ክፍል የትምህርት ጥራት ተቆጣጣሪ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
- በ6ኛው የኢፌድሪ የሕዝብ ተወካይ ም/ቤት የውኃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎች ልማትና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴመ ምክትል ሰብሳቢ
- በፓን አፍሪካ ፓርላማ አባል ሆኜ ተመድቤ የተሰጠኝን ኃላፊነት እንዲሁም ም/ቤቱ በተለያዩ ጊዜያዊ ኮሞቴዎች መድቦኝ ኃላፊነቴን በአግባቡ ተወጥቻለሁ፡፡
ከምንግሥት ሥራ ውጭ አገልግሎት
- ከመንግሥት ሥራ ውጭ የባህልና ተፈጥሮ ማህበር የተሰኘ ማህበር ከሌሎች ባልደረኖቼ ጋር በማቋቋም የድርጅቱ የፕሮጄክት ኃላፊ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡ በዚህን ወቅትም
o የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ-ምድር የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የዋናው የጥናት ቡድን ኮር አባል እና የፕሮጄክቱ ፕሮግራም መሪ ሆኜ የኮንሶ ባህላዊ መልክዓምድር የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘብ ካደረጉት ሦስት ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡
o ከዚህ በተጨማሪም አሁን የብሔረሰቦች ፌስቲቫል ተብሎ ሕዳር 29 የሚከበረው በዓል ከመጀመሩ በፊት በአርባምንጭ (አዋሳ፣ ዲላ፣ ሚዛን፣ ወልቂጤ እና አዲስ አበባ ጭምር) ለተከታታይ 3 (ሦስት ዓመታት) 1000 ኮከቦች ፌስቲቫል በሚባል ይታወቅ የነበረውን የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫል ዋና አዘጋጅና መሪ ሆኜ አገልግያለሁ፡፡
- በመጨረሻም በኮንሶ፣ በአፋርና በኦሞ የቅድመ ታሪክ ዓለም አቀድ የጥናትና ምርምር ፕሮጄክቶች አባል ሆኜ ለረዥም ዓመታት ሰርቻለሁ፡፡
- እንዲሁም በአፋር ክልልና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ፖቴንሻል የጥናት ፕሮጄክቶች ጥናት ሲካሄዱ በዋና አጥኚነት አገልግያለሁ፡፡
በእነኚህ የሥራ ዘመኖችም 3 (ሦስት) መጻሕፍትን እና በርካታ እርቲክሎችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎችና በአገር ውስጥ ጆርናሎችና ጋዜጦች አሳትሜያለሁ፡፡