የሕይወት ታሪክ

የግል የህይወት ታሪክ ሙሉ ስም፦ ወ/ሮ አዲስ ምትኩ ደስታ የአባት ስም፦ አቶ ምትኩ ደስታ የእናት ስም፦ ወ/ሮ ቦንቱ ጅሩ የትውልድ ቀን፦ 21/7/1976 ዓ.ም የትውልድ ቦታ፦ ም/ሸ/ዞን አዳማ ወረዳ አዱላላ ሐጤ ገ/ማህበር ዜግነት፦ ኢትዮጵያዊ የጋብቻ ሁኔታ፦ አግብቻለች የመኖሪያ ቦታ፦ አዳማ ከተማ ስልክ፦ 0911055320          የትምህርት ሁኔታ    እድሜው ለትምህርት ደረሰበት ጊዜ ከምኖረችበት ገጠር ቀበሌ ትምህርት ለማግኘት ወደ አዳማ ከተማ ብሎ ከ1984 እስከ 1993 ዓ.ም የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በአዳማ ከተማ አጠናቋል። በመቀጠልም ወደ አሶሳ ግብርና ኮሌጅ በመግባት 1997 ዓ.ም ዲፕሎማ ደረጃን ያገኘች ሲሆን፣ 1998 ዓ.ም በም/ሸ/ዞን አዳማ ወረዳ አዋሽ መልካሳ ገ/ማህበር የመንግስት አገልግሎት ጀምራለች። በስራ አፈፃፀም እና በታታሪነት ትኩረት ስትሰጥ የዲግሪ ት/ት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተሰጥቶት 2004 ዓ.ም በእንስሳት ሀብት (Animal Science) ዲግሪ ያገኘች ሲሆን፣ በህዋላም በተመሳሳይ የኦሮሚያ ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) የ6ኛ ዙር ሃገራዊ ምርጫ አባል የሆኑ ሴቶችን አቅም ለማጎልበት በተሰጠው የት/ት ዕድል ተጠቃሚ በመሆን ከኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Masters of Project Management) በ2016 ዓ.ም ማስተርስ ዲግሪ አግንቻለሁ። የግል ህይወት ከአቶ ደረጄ መንግስቱ ጋር በትዳር በመጣመር ሁለት ወንድ ልጆች አፍርታለች።  የወደፊት አላማ በቀጣይ በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ህዝቡ በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆኖ የሰጠውን ድምፅ እና አማና ከግብ ለማድረስ የህዝቡን የሰላም፣ የልማት እና የአብሮነት ጥያቄ በመረዳት ለህዝብ ተጠቃሚነት እና ብልጽግና ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት በትጋት እንሰራለሁ።