ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ አዱኛ አህመድ ኡሶ የተወለድኩት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ዳሮ ለቡ ወረዳ፣ ሚጨታ ከተማ ሲሆን።
የአንደኛ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርቴን በጭሮ ከተማ ነዉ የተማርኩት።
የመጀመሪያ የሕግ ዲግሪዬን (LL.B.) ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቀጠልም በሕግና ልማት(Law and Development) ልዩ ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ (LL.M.) ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ።
በሥራ ዘመኔ ያገለገልኩበት የሥራ ኃላፊነቶች፦
• በደደር ወረዳ እና በአዳማ ከተማ በዐቃቤ ሕግነት፣
• በኦሮሚያ የሕግ ሥልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሕግ አሰልጣኝና አማካሪ፣
• በኦሮሚያ ፍትሕ ቢሮ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣
• • በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በምክትል ደረጃ የሕግ አማካሪ፣
• በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ (Vice CEO) እና የሕግ አማካሪ፣
• በኦሮሚያ ሶቨርይን ፈንድ የሕግ ክፍል ዳሬክተርና አማካሪ፣
• እና አሁን በኦሮሚያ የሕግ ሥልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ።
• ባለፉት አምስት ዓመታት በፓርላማ ተወክዬ በፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ጉባአ አባል ሆኜ አገልግያለሁ።
• በተጨማሪም የኦሮሚያ ህገመንግስት አጣሪ ጉባአ አባል ሆኜ አገልግያለሁ።