የሕይወት ታሪክ

በቀለ ፎሌ እባላለሁ በቀድሞ ሲዳሞ ክፍለ ሀገር በሲዳማ አውራጃ አርቤጎና ወረዳ በ1958 ዓ.ም የተወለድኩ:: የአንደኛ እና መለስተኛ ደረጃ ትምህርቴን (1-8) በአርቤጎና ካጠናቀኩ በሁዋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን (9-12) በይርጋለም በለኩ እና በአለታ ወንዶ አጠናቅቂያለው:: የኮሌጅ ትምህርቴን የመጀመሪያ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ እና ሁለተኛ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አጠናቅቂያለው:: ሥራ ልምድን በተመለከተ በወረዳ የምክር ቤት ፀሐፊነትና በፅህፈት ቤት ኃላፊነት በሐዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሹምነት በዞን በሰው ኃይል ልማት ኤክስፐትነት እና ቡድን መሪነት አንዲሁም በመምሪያ ምክትል ኃላፊነት በክልል በከተሞች አደረጃጀት ባለሙያነት እና የከተሞች አደረጃጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመጨረሻም 2014 ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር አባል በመሆን ሀገርንና ሕዝብን በማገልገል ላይ እገኛለው::