ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ መምህርት ፅጌ የሽበር ደጌ በ1979 ዓ.ም. በዳባት ወረዳ፣ ጫርቢጣ ቀበሌ ተወለድኩ። የልጅነት ዘመኔን በትምህርት፣ በጠንካራ የቤተሰብ እሴቶችና በትርጉም ባላቸው ማህበራዊ ልምዶች በተቀረፀ አካባቢ አሳለፍኩ። እነዚህ የልጅነት ልምዶች የግል እድገቴን፣ እሴቶቼን እና ለትምህርትና ለሕዝብ አገልግሎት ያለኝን ቁርጠኝነት በመቅረፅ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። የትምህርት እድሜዬ ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በገደብጌ አንደኛ ደረጃና ጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀመርኩ፤ በዚያም የመጀመሪያና የጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በ1993 ዓ.ም. አጠናቀቅሁ። በመቀጠልም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በዳባት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ1995 ዓ.ም. አጠናቀቅሁ።
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴ በኋላ መምህርነትን እንደ ዋና የሙያ መስክ በመምረጥ በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የቋንቋ ትምህርት ተከታተልኩ። በ1996 ዓ.ም. የመምህርነት ሰርተፊኬት አገኘሁ፤ በመቀጠልም በመስከረም 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ዲፕሎማዬን አገኘሁ። የአካዳሚያዊ ዕውቀቴን የበለጠ ለማሳደግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የሰብዓዊ ሳይንስ ፋኩልቲ የኢትዮጵያ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርቴን በመከታተል በሰኔ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪዬን (BA) አገኘሁ። በተጨማሪም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ኮሌጅ የድህረ ምረቃ የመምህርነት ዲፕሎማ (Postgraduate Diploma in Teaching – PGDT) ትምህርቴን በመከታተል በጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም. አጠናቀቅሁ።
የአካዳሚያዊ እድገቴን በመቀጠል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የApplied Linguistics ዲፓርትመንት ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ ልዩ ትኩረት በመስጠት የMaster of Arts (MA) in Applied Linguistics የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቴን በመከታተል በጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. አገኘሁ። በአጠቃላይ፣ በአማርኛ ቋንቋ መምህርነት ከ21 ዓመት በላይ የሙያ ልምድ አካብቻለሁ። በዚህ የሙያ ጉዞዬ ወቅት ለበርካታ ትውልዶች ትምህርት በመስጠትና ለዕውቀታቸውና ለእድገታቸው አስተዋፅዖ በማድረግ የሚያኮራ ልምድ አግኝቻለሁ። ከመምህርነት ሥራዬ ጎን ለጎን የአካዳሚያዊና የሙያ እድገቴን በቀጣይነት በማሻሻል ከመምህርነት ሰርተፊኬት ጀምሬ እስከ ማስተርስ ዲግሪ ደርሻለሁ። በተመሳሳይ ጊዜም ሁለት ልጆችን ወልጄ በማሳደግ፣ የቤተሰብሃላፊነትን ተወጥቻለሁ፡፡
ሌላኛው ካለኝ የትምህርት ዝግጅት፣የስራ ተነሳሽነት ህዝባዊ ወገተኝነትና የአላማ ፅናት እና በብልጽግና ፓርቲ ሙሉ አባልነቴ ላይ በመመስረት በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በወገራ ወረዳ ቁጥር 2 ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆኜ ተወዳደርኩ። በምርጫውም ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ተመረጥኩ። በመመረጤ እጅግ ደስተኛ ሁኜ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በምሰጠኝ እንደ አንድ የተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የሚሰጠኝ ተግባርና ሃላፊነት ለመወጣት ሙሉ ዝግጅት አድርጌአለሁ፡፡ በዚህ በቀጣይ አምስት አመት የምክር ቤት አባልነት ቆይታየ ወክሎ የላከኝ ህዝብ መብቱ እና ጥቅሙ እንዲከበርለት መርህን መሰረት አድርጌ ላገለግለው ለራሴ ቃል ገብቻለሁ፡፡