የሕይወት ታሪክ

አ ጭር የህይዎትታሪክ ስመኝሽ ሳህሉ ጥዑም እባላለሁ ፤ከአባቴ ከቄስ ሳህሉ ጥኡም ከናቴ ከወይዘሮ ህብስቴ አድማስ መስከረም 1ቀን 1967 ዓ/ም በአማራ ክልል፤  አዊ ዞን፤ ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ጉሻ ሽንኩርታ ቀበሌተወለድሁ፡፡  እድሜየ ለትምህርት ሲደርስ በጉሻሽንኩርታ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት በ1974 ዓ/ም በመጀመር እስከ 5ኛ ክፍል ትምህርቴን ተከታተልሁ፤ ከዚያ በመቀጠልም በዚሁ ክልል ዞንና ወረዳ ቲሊሊ ከተማ ከ6ኛ አስከ 8ኛ ክፍል ከተከታተልሁ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን  በዚሁ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ትምህርቴን አጠናቀቅሁ፡፡  በመንግስት መስሪያቤት ተቀጥሬ እያገለገልሁ ዲፕሎማና የዲግሪ ትምህርቴን በርቀት በመከታተል ከአልፋ ዩንቨርስቲ ተመርቄያለሁ፤ ዲግሪየን ከያዝሁ በኋላ በመንግስት መስሪያቤት እያገለገልሁ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቴን በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደበደረማርቆስ ዩንቨርሲቲ ትምህርቴን አጠናቅቄለሁ ፤ በዚህ ሂደትም 16 አመት በተለያዩ መስሪያቤቶችና የሙያ መስኮች እንዲሁም 10 አመት በአመራርነት ህዝቤን እያገለገልሁ እያለ በ2013 ዓ/ም በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለፓርላማ ተወዳድሬ ብልጽግና ፓርቲን በመወከልና በማሸነፍ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እስከ 2018ዓ/ም መጨረሻ ድረስ ለተከታታይ 5አመታት ሳገለግል ነበር፤በተጨማሪም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዳግም ለፓርላማ ለመወዳደር እድሉ ስለተሰጠኝ ዳግም ተወዳድሬ በማሸነፌ ለቀጣይ 5 አመት የፓርላማ አባልል ሁኘ ህዝቤን እንዳገለግል እድሉተሰጥቶኛል በዚህም በጣም ደስ ብሎኛል እድለኛም ነኝ ለቀጣይ አመታትም ህዝቤን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፡፡                                                           አመሰግናለሁ                                                   1/13/2018                                                     አ/አ ኢትዮጵያ