የሕይወት ታሪክ

መአዛ አሰፍ እባላለሁ የተወለድኩት በ1985 እ.አ በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ሽክፍ ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን በኪሬ ደንቢያ እና በልእልት የሺመቤት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቄ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴንም በወረኢሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጨርሻለሁ :: የድፕሎማ ትምህርቴን በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ: የድግሪና የማስተርስ ትምህርቴን በወሎ ዮንቨርስቲ በማጠናቀቅ በለገሂዳ ወረዳ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ለይ አገልግያለሁ ባለበት 5 አመታት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የለገሂዳን ህዝብ የወከልኩ ሲሆን ለቀጣይ 5 አመትም ተመርጫለሁ ባለትዳርና የልጆች እናትም ነኝ::