ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ሞጋ አባቡልጉ አባካቤ በ 01/01/1971 አ.ም በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ አጋሮ ከተማ ተወለድኩ ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በአጋሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አጋሮ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተከታትያለሁ ። የመጀመሪያ ድግሪዬን በቢዝነስ ማኔጅመንት እንዲሁም ሁለተኛ ድግሪዬን(ማስተርስ) በብዝነስ አድሚኒስትሬሽን ሁለቱንም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ወስጃለሁ ።
የሥራ ዓለምን በተመለከተ በአጋሮ ከተማ የንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት ሐላፊ ፣ የማዘጋጃ ቤት ሐላፊ እንዲሁም የአጋሮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆኜ በቅንና ታማኝነት ሕዝቤን አገልግያለሁ ። በተጨማሪም የጅማ ዞን ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ሐላፊ ፣ የጅማ ዞን ፋይናንስ ፅ/ቤት ሐላፊ እንዲሁም የጅማ ዞን ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ሐላፊ ሆኜ በስኬታማነት አገልግያለሁ ። በአሁኑ ሰዓት የ6ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን በቅንነትና በታማኝነት እያገለገልኩ ሲሆን ለሁተኛ ጊዜም የ 7ኛ ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኜም ተመርጫለሁ ።