ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ቁጫ
ክልል:
ደቡብ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
እኔ ወ/ሪት ዓለሚቱ ዮሴፍ በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ ሞርካ ቀበሌ ከአባቴ አቶ ዮሴፍ ሳቃቶ እና ከእናቴ ወ/ሮ አቅሌ በላይነህ በቀን 20/01/1975 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡ ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል በሞርካ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በሰላምበር ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና 9ኛ ክፍል ሶዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ10ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል አርባ ምንጭ ሲቀላ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማርኩኝ፡፡ ከሰርተፊኬት ጀምሮ እስከ ማስተርስ የተማርኩ ሲሆን በብዝነስ አድሚንስትሬሽን 2ኛ ዲግሪ አለኝ፡፡ የሥራ ልምድን በተመለከተ ከጥር 1998 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ሥራ የተቀጠርኩ ሲሆን ከህዳር ወር 1999 ጀምሮ ከወረዳ ጽ/ቤት ም/ኃላፊነት እስከ ዞን መመሪያ ኃላፊነት እንዲሁም በቋሚ ኮሚቴነትና በክልል ም/ቤት አባልነት አገልጊያለሁ፡፡ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጋሞ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡