ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የተከበሩ አቶ ጋሻያለው ጋላ ጋላዳ
የህይወት ታሪክ
እኔ አቶ ጋሻያለው ጋላ ጋላዳ; ከአባቴ ከአቶ ጋላ ጋላዳ እና ከእናቴ ወ/ሮ ካኤኔ ካዝባ በዑባ ደብረፀሓይ ወረዳ በሆሻሌ ሻምባራ ቀበሌ መስከረም 04/1972 ዓ.ም ተወልድኩ።
ዕድሜዬ ለትምህርት ከደረሰ በኃላ በሆሻሌ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከ1-4ኛ ክፍል የተማርኩ ስሆን በአከባቢው የሚቀጥለው የክፍል ደረጃ ከአለመኖሩ የተነሳ ወደ በቶ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመሄድ ከ5-8ኛ ክፍል ትምህርቴን ተምራላሁ።
በመቀጠል ከ1986 ዓ.ም በወረዳው የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአለመኖሩ የተነሣ ወደ ጎፋ ዞን ሣውላ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምጣት ከ9-12ኛ ክፍል ለመማርችያለሁ።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ተፈትኜ ውጤት ከመጣ በኃላ በአርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የመምህርነት ሙያ በመማር በ1993 ዓ.ም የተመረቁ ስሆን በመቀጠል በደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የፊዚክስ ትምህርት በመማር ተመረቂያለው። ከዚያም በመቀጠል በአድማስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የመጀመሪያ ድግሪ ትምህርት ፣ በትምህርት አስተዳደር በመማር ተመርቄ ከ2004-2005 ዓ.ም ድረስ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ 2ኛ ድግሪ በመልካም አስተዳደርና በልማት ጥናት/Good Governance/ በመማር ተመርቂያለው።
የሥራ ሁኔታን በሚመለከት በመምህርነት ለ6 ዓመት፣ በወረዳ ፓርቲ ኃላፊነት እና በወረዳ ዋና አስተዳዳሪነት፣ በጋሞ ጎፋ ዞን ህዝብ ምክርቤት ጽ/ቤት ኃላፊነት፣ በጎፋ ዞን ህዝብ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት፣ በጎፋ ዞን ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊነት እና ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በ6ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የወረዳውን ህዝብ በመወከል የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል በመሆን ለ4 ዓመት አገልግዬ ከፓርቲ ዋና ጽ/ቤትና በክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት በተሰጠኝ ኃላፊነት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ።
በአጭሩ ለጊዜው የህይወቴ ታሪክ ይህንን ይመስላል፣ ሌሎችን ጉዳዮች ቀጣይ የእግዚአብሔር ፊቃድ ከሆነ በመካተት ሰፋ አድርገ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፣ አመሰግናለሁ!! እግዚአብሔር ይክበር!!