የሕይወት ታሪክ

የተከበሩ ወ/ሮ ዝናሽ ፀጋዬ ካሎ እባላለሁ፡፡የብልፅግና ፓርቲ አባል ነኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምኖረው በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 13 አፓርታማ ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ነው፡፡ የትምህርት ደረጃዬን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩንቬርሲቲ በባዮሎጂ የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘሁ ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው የኢስት አንግልያ ዩንቬርሲቲ በስርዓተ ፆታና ልማት የማስተርስ ድግሪ አግኝቻለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የስነ መለኮት ትምህር ቤት /ሴሚነሪየም/ በስልታዊ ስነመለኮት (Systematic Theology) የማስተርስ ድግሪ አግኝቻለሁ፡፡በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በባለሙያነት እና በሃላፊነት 28 ዓመት የስራ ልምድ ያለኝ ሲሆን በተለያዩ ድርጅቶች በቦርድ አባልነትና አመራርነት በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የበንሳና አከባቢው ሕዝብን ወክዬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነኝ፡፡ በ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በነበረኝ ቆይታ የጤና፣ ማህበራዊ እና ስፖርት ጉዳዮች እና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች አባል በመሆን አገልግያለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜም ለ7ኛው ዙር ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን ወክዬ በበንሳ የምርጫ ክልል በመወዳደር እና በማሸነፍ የምክር ቤት አባል ሆኘ የምቀጥል ይሆናል፡፡ በትርፍ ጊዜዬ መጽሐፍት በማንበብ፣ ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል፣ ማህበራዊ ሃላፊነቶችን በመወጣት እና የእግር ኳስ ጫዎታዎችን በመመልከት አሳልፋለሁ፡፡