የሕይወት ታሪክ

በአሁኑ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ሱጋሌ ቀበሌ ከአባቴ አቶ ወራሳ ጎድ እና ከእናቴ ከወ/ሮ ሲጴ በራሶ ሐምሌ ቀን 15/1950 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡ እድሜ ለትምህርት እንደደረሰ ወናጎ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት 1959 -1966 ዓ.ም ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተምሬ 8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተሸላም ሆኛለው፡፡ በ 1967 እስከ 1970 ዓ.ም በዲላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቴን አጠናቅቀዋለሁ፡፡ በመቀጠልም 12ኛ ክፍል እንደጨረስኩ ወደ ሥራ ዓለም በመቀላቀል ፊንጨዋ ገ/አገ/ሕ/ሥ/ማህበር የሂሳብ ሰራተኛ በመሆን ተቀጥሬ ከ1970 ዓ.ም እስከ 1990 ዓ.ም ድረስ ለ 21 ዓመታት ሰርቻለው፡፡ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ስርዓት ከፍተኛ ጫና በማሳደሩና፣ በህዝቡም ላይ ይደርስ የነበረው ስቆቃ አስከፊ ስለነበር የጌዴኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፓርት እንዲቀላቀል አደረገኝ፡፡ ድርጅቱን ከተቀላቀልኩ በኃላ የጌሕዴድ ማዕከላዊ አባል እና የወናጎ ወረዳ የጌሕዴድ ሰብሳቢ ሆኜ ለረጅም ጊዜያት አገልግያለው፡፡ ከድርጅቱ የተሰጠኝን ኃላፍነት እየተወጣው ያቆምኩትን ትምህርት በመቀጠል 1997 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ በሂሳብ አያያዝ ከ 2020 Open college ዲፕሎማ አግኝቻለው፡፡ ከዚያም በመቀጠል ከፓራዳይዝ ቫሊ ዩኒቨርሲቲ 2004 እስከ 2006 ዓ.ም በአካውንትንግ ድግርተመርቀዋለሁ፡፡ በተማርኩበት ሙያ በተለያዩ የግል ድርጅቶች ላይ በመቀጠር እየሰራሁ እገኛለው፡፡