ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ሐብሩ
ክልል:
አማራ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
• የተወለዱት የጁ (ወሎ) በ1964 ነው።
• ከ1972 እስከ 1983 ድረስ በሐብሩ ሊጎ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት፣ በጊራና አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት፣ በውርጌሳ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት፣ በወልድያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት፣ እና በወይዘሮ ስኂን (ደሴ) የቀለም፣ የቴክኒክ፣ እና የቮኬሽናል ትምሕርት ቤት ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ተከታትለዋል።
• የሦስተኛ ወይም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ሣይንስ በጀርመን አገር ከሚገኘው ገቲንገን ዩኒቨርሲቲ፤ የሁለተኛ ወይም የማስተርስ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክ ፖሊሲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የመጀመሪያ ወይም የባችለር ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
• በአሁኑ ወቅት:
o በአማራ ብሔራዊ ክልል የሐብሩ ምርጫ ክልል ሕዝብን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣
o የአማራ ብሔራዊ ክልል ጣና ሴክሬታሪያት ኃላፊ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚ ቴክኒካል አማካሪ፣
o በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተጣማሪ (አጄንክት) ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው።
• በአለፉት ጊዚያት፤
o በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ደረጃ፣
ከ2014 እስከ 2018 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ደሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣
ከ2016 እስከ 2017 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሃያ አምሥት ዓመት የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ (2018 – 2042) መሪ ፕላነር፣
ከ2014 እስከ 2016 የፕላን እና ልማት የኢኮኖሚ ቴክኒካል አማካሪ እና የተቋማት የእቅድ፣ የክትትል እና ግምገማ፣ የመንግሥት ልማት ኢንቨስትመንት አስተዳደር፣ እና የብሔራዊ ስታትስቲካዊ መረጃ አቅም ጥናት አጥኝ፣
ከ2012 እስከ 2013 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማ ልማት፣ የቤቶች፣ እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፣
ከ2011 እስከ 2012 በፕላን ኮሚሽን (የአሁኑ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር) ቴክኒካል አማካሪ፥የአሥር ዓመት የልማት ዕቅድ መሪ ፕላነር ሆነው የሠሩ ሲሆን፣
o በማስተማር፣ እና በጥናት እና ምርምር መስክ፣
ከ2002 እስከ 2011 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስየሽን የማክሮ ኢኮኖሚ ጥናት ክፍል ኃላፊ፣ ከፍተኛ ተመራማሪ፣ እና በተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች አስተማሪ እና አሰልጣኝ፣
ከ2010 እስከ 2016 በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተጣማሪ (አጄንክት) ተባባሪ ፕሮፌሰር፣
ከ2000 እስከ 2002 በጀርመን አገር በሚገኘው የቦን ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ እና መምሕር፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ ለውጥ ትምሕርት ክፍል የዲህረ ምረቃ ፕሮግራም አስተባባሪ፣
በ1992 በብሔራዊ ባንክ የኢኮኖሚ ምርምር ባለሙያ፣ እና
ከ1989 እስከ 1990 በሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ እና ማሕበራዊ ጥናት ቡድን ባለሙያ ሆነው አገልግለዋል።