ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የበላቸው አንሺሶ የህወት ታሪክ በአጭሩ
በላቸው አንሺሶ በሐዲያ ሆን በሌሞ ወረዳ ከቤቾ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ከአባቱ ከአቶ አንሺሶ ኬንቤጫና ከእናቱ ከወ/ሮ ሜሮ ሰዎሬ ጥር 10 ቀን 1965 ዓ.ም ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ አጠራር በሌሞ ወረዳ ፎንቆ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ም ቤት ተማሩ። በመቀጠል የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሆሳዕና ከተማ በሚገኘው የካቲት 25 መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምርትቤት አጠናቀቁ። ከዚያም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በዋቸሞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ም ቤት በ1978 ዓ.ም በማጠናቀቅ በወቅቱ አዋሳ መምህራት ትምህርት ኮሌጅ በመግባት በማምህርነት ሙያ በ1981 ዓ.ም በዲፕሎማ በማጠናቀቅ መንዝና ግሼ አውራጃ በመመደብ ደንገዜ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በጂኦግራፊ መምህርነት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በማገልገል ኢህአዴግ ሀገሪቱን ሲቆጣጠር ከመንዝ ወደ ትውልድ ቀዬያቸው በመዛወር ከ1983 እስከ 1987 ዓ.ም በሐዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።
ከዚያም በ1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ1991 በህግ የመጀመሪያ ድግሪ በመመረቀቅ በሀዲያ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ህግ በመሆን ለስድሰት ወር ያህል በማገልገል ከታህሳስ በ1991 እስከ ሚያዚያ 1993 ዓ.ም የሐዲያ ዞን ከፍጠኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ም/ሬዚዳንት በመሆን በታማኘነት አገልግለዋል።
ከሚያዚያ 1993 እስከ ጥር 2000 ዓ.ም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ተሹሞ የክልሉን ህዝብ በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል።
በህዝብና በሙያው ታማኝነት የተነሳ ጥር 1 ቀን 2000 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደኛ በመሆን ተሹሞ ለዘጠኝ ኣመታት ህዝብን በማገልገል ባሰየው ትጋትና ታማኝነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ተሹሞ በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ የሚታይና የሚቆተር የለውጥ ሥራ በደንብ ከተገበሩ ፕሬዚዳንቶች የመጀመሪያ ሰው ናቸው ብለው ዳኞች ይመሰክራሉ።
ወደ ዲፕሎማሲው ዓለም ከተቀላቀሉበት ከህዳር 2012 ዓ.ም ጀምሮ በጣሊያን ሮም የኢፌዴሪ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው በመመደብ ኤምባሲው በሚሸፍናቸው 10 አገራት በመንቀሳቀስ ከፍተኛ የዲፕሎማሲና የልማት ሥራ አከናውነዋል። በዚህም ለአገራችን ሁለት ዘመናዊ አምቡላንሶችን ከ10 በላይ አልትራሰውንዶችና መድኃኒቶችን በድጋፍ አስገኝተዋል።
በቤልጅየም ኤምባሲ በአውሮፓ ህብረትና በቤኔሉክስ አገራት የሚገኙ የዲያስፖራ ኮሙኒቲን በማስተባበር በአገራዊ የፖለቲካና የልማት ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ንቅናቄ በማድረግ ከፍተኛ የልማት እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲገኝ አድርገዋል።
የአራት ዓመት የውጭ አገር ተልዕኮአቸውን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ አጠናቅቀው ወደ አገር ቤት በመመለስ በውጨ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ መብትነጥበቃና ከለላ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን በዘርፉ የነበሩ የአሠራር ችግሮች በመፍታት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እና የአገራችንን ጥቅም በማስጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
በመንግሥት ኃለፊነት በቆዩባቸው ዘመናት የሙያቸውንና የሥራቸውን ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ በአገር ውስና ውጭ አገር የተላለየዩ አጫጭርና ረጃጅም የአመራርና የሙያ ሥልጠናዎችን ወስደዋል።
የአቶ በላቸው አንሺሶ አጭር የህይወት ታሪክ ይህን ይመስላል።