የሕይወት ታሪክ

አቶ ሰለሞን ሶካ አቶ ሰለሞን ሶካ ከጥር 2016 እስከ በአሁን ድረስ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሲሆኑ ወደዚህ የመንግስት የስራ ሃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶችና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትን በሃላፊነት መርተዋል። ሀገራቸዉንና ህዝባቸዉን በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል። እያገለገሉም ይገኛሉ። አቶ ሰለሞን ሶካ ወደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከመምጣታቸዉ ቀደም ብሎ የዕቅድ በጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የነበሩት ሲሆን በቋሚ ቆሚቴ ስራቸዉ ከፍተኛ የሚባል ተነሳሽነትና ለዉጥ በማምጣት ተቋማቱ ራሳቸዉን በለዉጥ ዉስጥ እንዲያሳልፉ እና ለዚጎች የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ምክረሃሳብ በመስጠት ባሻገር ባላቸዉ አቅም በመደገፍ ይታወቃሉ። አቶ ሰለሞን የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮንሶ ህዝብ ተወካይ ናቸዉ። አቶ ሰለሞን ሶካ በሁለት አስርት አመታት የስራ ቆይታቸዉ ለዉጥ ካመጡባቸዉና የአመራር አቅማቸዉ ተፈትኖ በብቃት ከተወጡባቸዉ ተቋማት መካከል፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) አንዱና ዋነኛዉ ነዉ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከህዳር 2014 እስከ ሃምሌ 2014 በምክተል ዋና ዳይሬክተርነት፤ አሁን በሃላፊነት እየሰሩበት ካለዉ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ እስከሆኑበት የካቲት 2016 ዓ.ም ድረስ ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከአንድ ዓመት ከ6 ወራት በላይ ህዝብና መንግስትን በታማኝነት አገልግለዋል። አቶ ሰለሞን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን በመሩበት ወቅት ከፍተኛ የሚባል የሪፎርም ስራ የሰሩ ሲሆን ለለዉጥ ካላቸዉ ቀናኢነት ዋና ዳይሬክተር ከመሆናቸዉ ቀድሞ ተቋሙ ለዉጥ እንደሚያስፈልገዉ በማመን ሲመሩት በነበረዉ ዘርፍ ለዉጥን በማድረግ ምሳሌ መሆን ችለዋል። ይህንንም ተቋሙን የመለወጥ ፍላጎታቸዉን ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ሲመደቡ ተቋማዊ ያደረጉት ሲሆን ተቋሙን በመፈተሽና ከከፍተኛ አመራር እስከ ሰራተኛ ድረስ ተቋሙ በገጠሙት ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር በማድረግ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ሪፎርም የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚፈለገዉ ልክ ለማስጠበቅ አስፈላጊነቱን በዉል በመረዳት በከፍተኛ አመራር ሰጭነትና ክትትል፣ ሃሳብ አመንጪነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ተቋማዊ ለዉጥ መርተዋል። በዚህ የሪፎርም ስራቸዉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከሀገራዊ ተልዕኮ ጋር የተጣጣመ፣ በመንግስት የሚሰጡትን ሀገራዊ ሃላፊነቶች በብቃት የሚወጣ፣በህዝብ ዘንድ ያለዉን ተቀባይነትና ታማኝነት በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ የሚባሉ ትብብርና አጋርነቶች እንዲፈጠር የማድረግ ስራ ሰርተዋል። ከዚህ ባሻገር ህዝቡ ለመረጃና ደህንነት ተቋማት ማህበረሰቡ ያለዉን የተዛነፈ ምልከታ በማስተካከል ደረጃ በተሰሩ የገጽታ ግንባታና ተቋማዊ ትብብሮች ላይ ምስጉን ስራ የሰሩት አቶ ሰለሞን ካላቸዉ የአዉዱ እዉቀትና ግንዛቤ በመነሳት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በተሰራዉ ስዉር ዉጊያ ፊልም ዉስጥ ሃሳብ በመስጠት፣ አቅጣጫ በማሳየትና ከፊልሙ ዳይሬክተር ያልተናነሰ፣ ከጸሃፊዉ ሃሳብ የላቁ የሳይበር ምህዳሩን ተግዳሮትና መልካም እድሎች ላይ ሃሳብ በመሰንዘር የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር የቻል ፊልም በማዉጣት ሂደት ዉስጥ የላቀ ድርሻ ተወጥተዋል። አቶ ሰለሞን የመደመር ጽንሰ ሃሳብ በተነሳበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የመጀመሪያዉ ትዉልድ አካል ሲሆኑ የአሁኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢመደአን በሚመሩበት ወቅት የመደመርን ጽንሰ ሃሳብ ከመነሻዉ ጅምረዉ የተረዱና የተገበሩ ናቸዉ። ይህ የመደመር እሳቤያቸዉ በሃላፊነት በሰሩባቸዉ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ ተግብረዋል። አቶ ሰለሞን ስራዎችን አስተባብሩ በመስራት፣ ተለዋውጭ ሁኔታዎችን የመረዳት፣ አዳዲስ ጉዳዮችን በፍጥነት የመማርና የመተግበር እንዲሁም በመደመር እሳቤ የሚያምኑና የሚተገብሩ ናቸዉ። ከዚህ ባሻገር አቶ ሰለሞን ሶካ ከፍተኛ የሚባል ለሀገርና ለፓርቲያቸዉ ዉግንና ያላቸዉ ሲሆን ካላቸዉ የፖሊቲካ ታማኝነት ባሻገር ለኢትዮጵያ እድገትና ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ የሚባል ቀናኢ ናቸዉ። በዚህም በሚመሩት የኮንሶ ማህበረሰብ አካባቢ የተፈጠሩ የሰላም እጦቶች እንዲስተካከሉና በጎሳዎች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በዉይይት እንዲፈታ በመጣር ለዞኑ፣ ለክልሉ እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ደህንነት የበኩላቸዉን ሚና ተጫዉተዋል። አቶ ሰለሞን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የህብረቤራዊነት ማሳያ ሲሆኑ ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለህብረብሄራዊ ተቋምነት የሚያደርገዉን ጥረት ማሳያ ከመሆን ባሻገር በተቋም ሪፎርም ስራቸዉ ህብረ-ብሄራዊነትን አጥብቀዉ የሚናገሩና የተገበሩ የለዉጥ ሃዋሪያ ናቸዉ። የሀገር አቀፍ ጸረ-ሙስና ግብረሃይል ኮሚቴ አባላ ሆነዉ ያገለገሉት አቶ ሰለሞን መንግስት ለልማታችንና እድገታችን ነቀርሳ የሆነዉን ሙስናን ለመከላከል ባደረጋቸዉ እንቅስቃሴዎች የላቀ ሚና ተጫዉተዋል። አቶ ሰለሞን ሶካ ወደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከመምጣታቸዉ ቀደም ብሎም በቴክ ማሂንድራ በተባለ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ከፕሮግራም ማናጀርነት እስከ ካንትሪ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። ካላቸዉ ነገሮችን የማወቅና ክፍት የሆነ አዕምሮ ያላቸዉ፣ ቶሎ የመላመድና አዉዳዊ የመሆን አቅማቸዉ አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቋም የመምራት እድል አስገንቶላቸዋል። ይህን እድልም በብቃት መወጣት ችለዋል። ዓለም አቀፍ ደረጃ በሃላፊነት ሰራ ከመስራታቸዉ ቀደም ብሎም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከባለሙያ እስከ ምክትል ዳይሬክተር የስራ ሃላፊነት ያገለገሉት አቶ ሰለሞን በስራ ልምዳቸዉ ካካበቱት እዉቀቶችና ከሚመሰገኑበት ስራዎች መካከል ለለዉጥ ያላቸዉ ቀናኢነት ለዉጥን የመምራት ብቃታቸዉ ነው። አቶ ሰለሞን ሶካ ሁለት አስር አመታት በቆየዉ የስራ ልምዳቸዉ ከባለሙያነት እስከ ሚኒስቴር ድዔታነት የደረሱ ሲሆን የዳታ ቤዝ ምህንድስና፣ የሶፍትዌር ልማትና አስተዳደር፣ የመረጃ ስርዓት ትግበራ ፕሮጀክት/ፕሮግራም አስተዳደር ላይ፣ የንግድ ልማት ስራ ላይ፣ የሰዉ ሃይል ልማትና አስተዳደር፣ በርካታ አቅም ፈጥረዋል። በተሰማሩበት መሰክ ሁሉ ምስጉን ሆነዉ ያገለገሉ ሃገር ወዳድ ዜጋ ናቸዉ። በሃላፊነት ቆይታቸዉም ባለድርሻ አካላት አስተዳደር እንዲሁም ስትራቴጂያዊ አስተዳደር እና አመራር ላይ ያላቸዉን እዉቀት በመጠቀም ለዉጥ ማምጣት ችለዋል። በትምህርት ዝግጅታቸዉ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸዉን ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ያገኙት አቶ ሰለሞን ሶካ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሶፍትዌር ምህንድስና ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ1998 አጠናቀዋል። በዚሁ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲፕሎማ ከመያዝ አልፈዉ በዚሁ ኮሌጅ በመምህርነት አገልግለዋል። አቶ ሰለሞን የተለያዩ ክህሎቶች ባለቤት ሲሆኑ ከእነዚህ ክህሎቶች መካከልም፦ በዓለም አቀፉን ኮርፖሬት መቀላቀላቸዉን ተከትሎ ሰፊ የስራ ልምዶችን እና ክህሎቶችን ያዳበሩ ሲሆን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ካካበቱት ቴክኒካል እውቀት በተጨማሪ በቢዝነስ ልማቶች ላይ ከፍተኛ የሚባል ክህሎቶችን መገንባት ችለዋል። በቴክ ማሂንድራ ሆነ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የስራ ሃላፊነት ቆይታቸዉ ለተቋማቱ የሚጠቅሙ የተለያዩ ስምምነቶችን በመፍጠርና ተቋማዊ ለዉጦችን በመምራት ትርጉም ያለዉ ስራ መስራት ችለዋል። ለዉጥን የመምራት ከፍተኛ አቅም በመጠቀም ስትራቴጂክ ቡድኖችን በመፍጠር፣ በመገንባት እና በመምራት ከፍተኛ ችሎታ ማዳበር የቻሉ ሲሆን ዉጤታማ የሚባሉ ቲሞችን በመፍጠር፣ የባለድርሻ አካላት አስተዳደር ላይ፣ አጋርነትን/ግንኙነትን በማጠናከርና በመምራት፣ ለዉጦችን በማማከር፣ በፕሮጀክት/በፕሮግራም አስተዳደር ላይ ላቅ ያላ አቅማቸዉን በተለያዩ የሃላፊነት ቆይታቸዉ አሳይተዋል። ከቴክኒካል እዉቀታቸዉ ስፊ ልምድ ያላቸዉ ሲሆን በኢንተርፕራይዝ ሲስተም ዲዛይንና አተገባበር፣ በኦራክል የዳታ ቤዝ አስተዳደር ሰፊ እዉቀቶችን አካብተዋል። በሶፍትዌር ልማት ላይም ከፍተኛ የሚባል እዉቀቶችን የሰበሰቡት የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ውስብስብ እና የቅርብ ጊዜ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ምህዳርንና የመረጃ ስርዓቶችን አተገባበር እንዲሁም መረጃ ስርዓት ዲዛይን እንዲሁም የጥናትና ምርምር እንዲሁም ልማት ዘርፍ ላይም ሰፊ እዉቀት አዳብረዋል። አቶ ሰለሞን ካላቸዉ ዋና ዋና ክህሎቶች መካከልም፦ ክኒካል ክህሎት፣ የአመራር ክህሎት ፣ የአስተዳደርና ማናጅመት ክህሎት፣ በቡድን የመስራት ክህሎት እንዲሁም የተግባቦት ክህሎቶች ቀዳሚዎቹ ናቸዉ። አቶ ሰለሞን ሶስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈዉ የሚናገሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ የሆነዉን ኮንስኛን ጨምሮ አማረኛና እንግሊዘኛ ተናጋሪ ናቸዉ።