የሕይወት ታሪክ

ሰላማዊት ካሳ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ተወልዳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን በመከታተል በስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝታለች። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቱሪዝም ሚኒስትር ሆና እያገለገለች ሲሆን፣ ከአስር ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት፣ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን እና በሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች ሰፊ ልምድ አላት። ከዚህ በተጨማሪም የመንግሥት ቃል አቀባይ ሆና አገልግላለች፤ በቱሪዝም ልማት፣ በባህልና ቅርስ ጥበቃ፣ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የምስል ግንባታ እና በስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ዘርፎች ሰፊ ልምድ አላት።