የሕይወት ታሪክ

በ1968 ዓ,ም በስዳማ ዞን በዳራ ወረዳ ተወለድኩኝ። እድሜዬ ለትምህርት ስደርስ ከአንደኛ ክፍል እስከስድስተኛ ክፍል በስዳማ ዞን በዳራ በረዳ ቡና ጣዋባ ትምህርት ቤት ተምሬ ወደ ሰባተኛ ክፍል ተዛወርኩኝ። የ7ኛ ክፍል ትምህርቴን እስከ 8ኛክፍል ድረስ በስዳማ ዞን ተፈሪ ኬላ መለስተኛ ትምህርት ቤት ከተማርኩኝ ቦኋላ ሚኒሲትሪ ተፈትኜ ወደ ዘጠነኛ ክፍል ከተዛወርኩኝ ቦኋላ በወቅቱ በወረዳ ሀይስኩል ባለመኖሩ የተነሳ ከዘጠነኛ ክፍል እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ በአጎራባች በጌደኦ ዞን ዲላ ሀይስኩል አጠናቀኩኝ። የአሥራ ሁለተኛ ክፍል (ማትሪክ) ውጤቴ ለመምህርነት ሙያ በቂ ስለነበረ ተወዳድሬ በአሁኑ በሀዋሳ መምህራን ኮለጂ በቀድሞ TTI ሰልጥኜ ተመረኩኝ።ከዚያ ቦኋላ እራሴን ለትምህርት በማዘጋጀትእና በመማር በብዙ ጥረትና ትጋትየትምህርት ደረጃዎቼን ለማሻሻል ችያለሁ።