የሕይወት ታሪክ

ር እሸቱ ገ/ማሪያም ጉል እባላለሁ ። ከአፍሪካ እና ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችው አዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር በላይ ርቃ ከምትገኘው፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ -ማጂ ከተማ በ1975 ዓ.ም የተወለድኩ ሲሆን፣ ይህ የትውልድ ቦታዬ እና ህብረተሰብ ለህይወቴ ጉዞ መሠረታዊ ሚና ተጫውቷል። የተወለድኩት በማጂ ከተማ 01 ቀበሌ ሲሆን፣ ወላጆቼ መምህር አቶ ገብረማሪያም ጉል እና ወ/ሮ ከበቡሽ ወርቁ ናቸው። በትምህርት የታነጸ ቤተሰብ ውስጥ ማደጌ ለትምህርት ፍቅር እና ለአገልግሎት መንፈስ መሠረት ጥሎልኛል። ከወ/ሮ ሀረገወይን አበበ ሮቢ ጋር ትዳር መስርቼ 3 ልጆች አባት ሆኛለሁ። ትምህርቴን በዲፕሎማ ደረጃ በዕፅዋት ሳይንስ ጀምሬ፣ በኋላም የመጀመሪያ ዲግሪዬን በኢኮኖሚክስ፣ ማስተርስን በከተማ ልማት ስራ አመራር፣ እንዲሁም ዶክትሬትን በኢኮኖሚክስ በማግኘት የትምህርት ጉዞዬን ቀጥያለሁ። ይህ የትምህርት መንገድ ለሙያዬ እና ለአገልግሎቴ ጠንካራ መሠረት ፈጥሮልኛል። ከ20 ዓመት በላይ በኃላፊነት እና በሞያዮ ሀገሬን አገልግያለሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር የፓርላማ አባል ሆኜ በመምረጥ፣ የከተማ፣ መሠረተ ልማት፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግያለሁ። ለ7ኛው ዙርም በህዝብ በመመረጥ አገልግሎቴን እየቀጠልኩ ይገኛል ። ሳጠቃልል ከማጂ ከተማ የተነሳው የህይወቴ ጉዞ፣ በትምህርት፣ በኃላፊነት ፣ በሙያ እና በህዝብ አገልግሎት የተሞላ ሲሆን፣ የትውልድ ቦታዬ እናህዝብ ለዚህ ሁሉ ስኬት መሠረት ሆኖልኛል። ከ700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ካለችው ማጂ ተነስቼ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ለህዝብ አገልግሎት መድረሴ የትውልዴ ቦታ ምንም እንኳን ርቃ ብትገኝም፣ ለስኬት እና ለአገልግሎት መንገድ እንደማይከለክል ያሳያል።