በህዝብ ውክልና ስራ የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸው ተገለጸ

 (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 19 ቀን 2017 .ም፤ አዲስ አበባ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች /ቤት ባካሄደው 40 መደበኛ ስብሰባው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር 2017 በጀት ዓመት 11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (/) የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የሕዝብ ተወካዮች /ቤት አባላት በየካቲት ወር 2017 . ወደ ምርጫ ክልላቸው በሄዱበት ወቅት ከመንገድ ደህንነት፣ ከህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት፣ ከትራንስፖርት ታሪፍ፣ ከአነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ፣ ከመናኸሪያ፣ ከደረቅ ወደብ ግንባታና በህገ-ወጥ ኬላዎች ዙሪያ በተያያዘ ከህብረተሰቡ ለተነሱ 46 ለሚሆኑ ጥያቄዎች በዝርዝር በማየት ምላሽ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

የሚኒስቴር /ቤቱ ዋነኛ ተልዕኮ የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ቀርፆ ሥራ ላይ በማዋል የአገሪቱን ኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገትን የሚያፋጥን፣ ተደራሽ፣ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ አስተማማኝ፣ የመክፈል አቅምን ያገናዘበ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት ሥርዓትን በመዘርጋት የህብረተሰቡን ፍላጐት ማሟላት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ዘርፉ ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን ሁሉ እያበረከተ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ፤ በዚሁ መሠረት ባለፉት አስራ አንድ ወራት ሚኒስቴር /ቤቱ የሴክተሩን ተቋማት እና ክልሎችን በማቀናጀትና በማስተባበር ይህንን ወሳኝ ተልዕኮ ቀጣይነት ባለው አግባብ ለማሳካት በትኩረት ርብርብ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ሚኒስቴር /ቤቱ በስድስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አትኩሮ መስራቱንም ገልጸዋል፡፡

የተከናወኑት አበይት ተግባራትም ተቋማዊ አቅም መገንባት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ የዘርፉን ውጤታማነት ማረጋገጥ፤ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የትራንስፖርት አገልግሎቱን መሠረተ ልማት የተቀናጀ ፍትሀዊ እና ተደራሽ እንዲሆን ተባብሮ መሥራት እና የሎጀስቲክስ አገልግሎቱን ቀልጣፋና አስተማማኝ ማድረግ መሆናቸውንም ነው ክቡር ሚኒስትሩ ያመላከቱት፡፡

በዚህም በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ 913 ሚሊየን ሕዝብ ለማጓጓዝ ታቅዶ 960 ሚሊዬን ህዝብ በማጓጓዝ ከእቅድ በላይ መፈጸም መቻሉን፣ የአንድ አገር አቋራጭ አውቶብስ አማካይ ዓመታዊ ኪሎ ሜትር ሽፋን በዓመቱ 107 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማድረስ ታቅዶ 105 ሺህ ኪሎ ሜትር በማድረስ ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡንም በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በአየር ትራንስፖርት የመንገደኛ አገልግሎትን ማሻሻልን በተመለከተ የሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት መዳረሻዎችን ቁጥር 23 ወደ 26 ማሣደግ መቻሉ፣ የሀገር ውስጥ መንገደኞችን ቁጥር ወደ 17.3 ሚሊዬን ለማድረስ ታቅዶ 13.5 ሚሊዬን በማድረስ ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በአየር ትራንስፖርት የተፈረሙ አለም አቀፍ ስምምነቶችን 110 ወደ 113 የአውሮኘላኖች ብዛትን 178 ወደ 190 የአለም አቀፍ መዳረሻ ቦታዎችን 138 ወደ 155 ለማሳደግ እና 89.3 ሚሊዬን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ታቅዶ 111 ሥምምነቶችን መፈራረምና የአውሮኘላኖችን ቁጥርም 183 ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የአለም አቀፍ መዳረሻዎችን 143 ማድረስ እና 75.2 ሚሊዬን መንገደኞችን በማጓጓዝ የእቅዱን 89.3% መፈጸም መቻሉንም አክለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (/) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማዘመን የዲጂታላይዜሽን ስራዎች መተግበራቸውን፣ ደንቦች፣ መሪያዎችና የአገልግሎት አሠጣጥ ደረጃዎች ጥናት ሰነዶች ፀድቀው በስራ ላይ መዋላቸውንም ነው ያብራሩት፡፡