የአፈ - ጉባኤ ምርጫ

የሹመት ዓይነቶች በሶስት እንደሚከፈሉ የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 105 ያሳያል፡፡ ከነዚህ የሹመት ዓይነቶች አንዱ ‘’መመረጥ‘’ ነው፡፡ ይህም ቃል የሚሰራው ለምክር ቤቱ አፈ - ጉባኤ እና ምክትል አፈ - ጉባኤ  መመረጥ  ነው፡፡  መነሻውም የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 19 ነው፡፡  ይህ ንዑስ አንቀጽ ምክር ቤቱ ‘’ምክር ቤቱን የሚመሩ አፈ - ጉባኤና ምክትል አፈ - ጉባኤ ይመርጣል‘’ ስለሚል ነው፡፡  
ይህን ‘’መመረጥ‘’ የሚለውን ቃል ከደንቡ አንቀጽ 8 አንጻር ሲታይ ዕጩ አፈ - ጉባኤ እና ምክትል አፈ - ጉባኤ የሚጠቆመው በማንኛውም የምክር ቤት አባል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ጥቆማ በአንድ ሌላ አባል መደገፍ ይኖርበታል፡፡ ዕጩ ተጠቐሚውም ሃላፊነቱን ለመቀበል ፈቃደኝነቱ ይጠየቃል፡፡ ፈቃደኛ ሆኖ ከተገኘ  ምርጫውን በሚያስፈጽመው አካል በዕጩነት ይመዘገባል፡፡
ሌሎች ተጠቐሚዎች ካሉ በደንቡ አንቀጽ 8/3/ መሰረት ‘’የተጠቆሙ ዕጩዎች ስም ዝርዝር በፊደል ተራ ይመዘገባል፤ በዚሁ ቅደም ተከተል መሰረትም ድምጽ ይሰጣል፤‘’  8/3/ መሰረት አባላጫ ድምጽ ያገኘ ዕጩ አባል አፈ - ጉባኤ  ይሆናል፡፡‘’ ተመሳሳይ ስርዓትም ለምክትል አፈ - ጉባኤ ምርጫ ይተገበራል፡፡
ድምጽ መስጠቱ አንድ ዕጩ አባል ብቻም ከቀረበም የማይቀር ሂደት ነው፡፡  አባላጫ ድምጽ ላገኘ ብቸኛ ዕጩ ተወዳዳሪ አፈ - ጉባኤ ወይም ምክትል አፈ - ጉባኤ አይሆንም፡፡  ሌላ ዕጩ አባል የግድ መቅረብ ይኖርበታል፡፡  አባላጫ ድምጽ  መገኘቱም የወጣ እጅ በመቁጠር  እንደሚረጋገጥ አንቀጽ 8/3/  ያመለክታል፡፡
ከአንድ በላይ ዕጩ ቀርቦ ከሆነ ‘’ምርጫው በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ‘’ እንደሚከናወን የደንቡ አንቀጽ 8/3/ ይደነግጋል፡፡
ስለዚህ ‘’መመረጥ‘’ ሚለው ቃል   አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ - ጉባኤ በምክር ቤት አባላት ተጠቁመው በምክር ቤት በመመረጥ ለምክር ቤቱ ተጠሪ  ሆነው ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ  ያመለክታል፡፡  በምክር ቤቱ የቃሉ ትርጓሜ ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55/19 እና ከደንቡ አንቀጽ 8 ጋር ተገናዝቦ የሚታይ ነው፡፡
‘’መመረጥ‘’ ጊዜ  ዕጩ አፈ - ጉባኤ እና ዕጩ ምክትል አፈ - ጉባኤ የማቅረብ ብቸኛ  የስልጣን  ባለቤት የማንኛውም የምክር ቤት አባል እንደሆነ የደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 8/3/ ይደነግጋል፡፡  ይህ መብት ለማንም  ሌላ አካል አይተላለፍም፡፡  ለእያንዳንዱ የምክር ቤት አባል የተሰጠ መብት ነው፡፡ መሰየም ደግሞ በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ላገኘ የፖለቲካ ፓርቲ የተሰጠ ብቸኛ መብት ነው፡፡
 

የተከ.  ዶ/ር ጴጥሮስ ኦላንጎ ዱቡሾ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ :- አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት፡- ሳኬ አድቬንቲስት ት/ት ቤት - ሁለተኛ ደረጃ፡- ሻሸመኔ ኩዬራ አድቬንቲስት ት/ት ቤት - ከፍተኛ ትምህርት፡- • ከጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እኤአ 1984/5 በህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ • ከአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ፉኩልቲ እኤአ በ1989 በህዝብ ጤና አጠባበቅ የማስተርስ ዲግሪ • ከአመስተርዳም ዩኒቨርሲቲ እኤእ በ2000 በዓለም አቀፍ ህግ የማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
Experience

የስራ ልምድ - በሆስፕታል ሀኪምነት 1978/79 - የአውራጃ ጤና ጥበቃ ሃላፊነት 1980/81 - የምዕራብ ሸዋ ጤና መምሪያ ሃላፊ 1981/85 - የደቡብ ጤና ቢሮ የፕላንና ፕሮግራም ሃላፊ/1985/87 - ከነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም --- መስከረም 30 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ - ብዙ የስራ ላይ ስልናጠናዎችን የወሰዱ እና ብዙ የባለብዙ ወገን የፓርላማ መድረኮችን የተሳተፉ ብዙ ልምድ ያካበቱ ባለስልጣንና ፖለቲከኛ ናቸው፡፡

የተከበሩ አቶ ዳዊት ዮሐንስ
Education Level: -----
Experience

ከነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ. ም --- መስከረም 28 ቀን 1993 ዓ.ም

የተከ. ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ትዕዛዙ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - አንደኛ ደረጃ፡- አዴት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ሁለተኛ ደረጃ፡- ጣና ሀይቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ከፍተኛ ትምህርት ፡- • ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፔዳጎጂካል ሳይንስ በባችለር ዲግሪ በ1982 ዓ.ም ተመርቀዋል • ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰርዓተ ትምህርትና በማስተማር የማስተርስ ዲግሪ በ1993 ዓ.ም ተመርቀዋል፡፡
Experience

የስራ ልምድ - ከ1982 – 19844 ዓ.ም ሮቤ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም መምህር - ከ1985 – 1988 ዓ.ም ደብረወርቅ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት መምህር - ከ1989 – 1992 ዓ.ም የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ የጂኦግራፊ ኤክስፐርት/ካሪኩለም/ - ከ1993 – 1997 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል - ከ1998 – 2002 ዓ.ም ምክር ቤቱ አባልና ምክትል አፈ ጉባኤ - ከ2003 – 2007 ዓ.ም የምክር ቤቱ አባልና ምክትል አፈ ጉባኤ - ከ2008 – 2013 ዓ.ም የምክር ቤቱ አባልና ምክትል አፈ ጉባኤ - በምክር ቤት ቆይታቸው የተመራጭ ሴቶች ኮከስን በመምራት የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል - የፓን አፍሪካ ፓርላማ የኢትዮጵያ ልዑክ መሪ በመሆን በመድረኩ የኢትዮጵያን ጉዳይ በማስተዋወቅና የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባታ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

የተከ. አቶ አባዱላ ገመዳ
Education Level: - በቻይና የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ወታደራዊ አመራር ትምህርት ተከታትለዋል - ከአሜሪካ ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቱ በህዝብ አስተዳደር በ2001/እኤአ/ የመጀመሪያ ዲግሪ እና በ2004/እኤአ/ የሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል - ሌላ ሁለተኛ ዲግሪ ከእንግሊዝ አገር ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በ2009 /እኤአ/ አግኝተዋል
Experience

በወታደራዊ መስክ - ኢህአዴግ ወደሥልጣን ከመጣ ከ1983 ጀምሮ እስከ 1988 ለ5 ዓመታት የወታደራዊ ስምሪት ዋና ሃላፊ - ከ1988 እስከ 1990 ዓ.ም ለሁለት ዓመት የወታደራዊ ደህንነት ዋና ሃላፊ - ከ1990 እስከ 1993 ዓ.ም የምድር ጦር ዋና አዛዥ - ከ1993 እስከ 1997 ዓ.ም የመከላከያ ሚኒስትር እና በዚህ ሃላፊነት ውስጥ እስከ ሜጀር ጀኔራል ማዕረግ ደረጃ ድረስ አድገዋል በሲቪል መስክ - ከ1998 እስከ 2003 ዓ.ም መስከረም መጨረሻ ድረስ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከህዝብ ዘንድ አክብሮትና ተወዳጅነት ነበሯቸው፡፡ ይህንን ያልወደደላቸው የቁንጮ ሰዎች በሃላፊነቱ ቦታ የመድገሙን ዕድል እንደነፈጓቸው በወቅቱ ይነገር ነበር፡፡ ለምን የሚሉ ጥያቄዎችን ለማፈን የግምገማ መድረክ መፈጠሩን የጠቆሙ የውስጥ አዋቂዊችም ነበሩ፡፡ - ከ2008 መስከረም እስከ 2010 ዓ.ም መጋቢት ወር ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ሰርተዋል፡፡ ምክር ቤቱን በበላይነት ከመምራት ባሻገር የተለያዩ ቦርዶችንም በሃላፊነት መርተዋል ምክር ቤቱ የኦዲት ግኝቶች እንዲስተካከሉ ኮሚቴ አቋቋሞ እንዲንቀሳቀስ የመሪነት ሚና ተጫውተዋል፡፡ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ይፋ መደረግ ገንዘብ ጠፋ ማለት አይደለም የሚል የብስጭት መግለጫ የወቅቱ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን ማውጣቸው የሚታወስ ነው፡፡ በምክር ቤቱ ውስጥ ንቅናቄ የማስጀመራቸው አንዱ ምልክት ይህ የኦዲት ግኝትን ለማስፈጸም ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ አቶ ዳዊት ዮሐንስና አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የጣላቸውን የምክር ቤት አባላት ለማንሳትም ታግለዋል፡፡ ተሰናባች የምክር ቤት አባላት እንደመብት በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤት ማግኘት የጀመሩት በእሷቸው ጊዜ ነው፡፡ እንደዚሁም የመቋቋሚያ አበል ክፍያ ለአንድ ምክር ቤት ዘመን የ7 ወር ደመወዝ የነበረውን ወደ11 ወር አሳድገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ላገለገሉ የምክር ቤት አባላት ጣሪያው የ18 ወር ደመወዝ የነበረውን ወደ24 ወር ደመወዝ አሳድገዋል፡፡ ከዚህ መቋቋሚያ አበል ይቆረጥ የነበረውን 35 በመቶ ታክስም አስቀርተዋል፡፡ አባዱላ ገመዳ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፈ ጉባኤነት እንዲቀርቡ በዶር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በዕጩነት ሲጠቆሙ ሙሉ ስማቸውን ጠቋሚው አንብቦ ሳይጨርስ የተቀበላቸው የወንዱ ጭብጨባና የሴቱ ዕልልታ እንኳን አዳራሹ ውስጥ ያለውን ሰው ቀርቶ በምክር ቤቱ ግቢ ያለውንም ሰው ያስገረመና ያስደመመ ነበር፡፡ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት በነበሩ ጊዜ በህዝቡ ይወደዱ ነበር ለሚለው ዜና ይህ የምክር ቤት አባላት ሁኔታ ጥሩ ማረጋገጫ ሳይሆን አልቀረም፡፡ የምክር ቤት አባላት በደል ‘’በኔ ጊዜ ይቁም’’ የሚል መርህ ይዘው ይሰሩ እንደነበሩ ያስመስላቸዋል፡፡ መጋቢት 2010 ከምክር አፈ ጉባኤነት ከተነሱ በኋላ ለአጭር ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆነው የሰሩ ሲሆን አሁንም በዚያ አካባቢ በመሆን ከመስራት ባሻገር በጎ አድራጎት ድርጅት በማቋቋም አገራቸውንና ህዝባቸውን በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በሃሳባቸው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

የተከ. ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
Education Level: የትምህርት ሁኔታ፡- ከፍተኛ ትምህርት እኤአ በ2000 ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በእርሻ ሳይንስ የመጀመሪ ዲግሪ ተመርቀዋል - በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል
Experience

የስራ ሁኔታ - እኤአ በ2007 የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት አማካሪ - እኤአ በ2008 የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር - ከ2003 --- 2007 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ - ከ2008 --- 2014 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - በሚኒስትር ማዕረግ በዴሞክራቲክ ግንባታ ማዕከል የምርምርና የፓብሊኬሽን ሃላፊ የመለስ አመራር አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚያዚያ 11/2010 --- ጥቅምት 8/2011 ዓ.ም ድረስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ከጥቅምት 6/2011 --- መስከረም 26/2014 ዓ.ም ድረስ የሰላም ሚኒስትር ከመስከረም 26/2014 ዓ.ም ጀምሮ የሥራና ክሂሎት ልማት ሚኒስትር ምክር ቤቱ ውስጥ ያደረጉት አስተዋጽኦ - የምክር ቤቱን ሕንጻ በማደስ ለስራ ምቹ አድርገዋል - የተለያዩ የሞባይል አፕሊኬሽኖች እንዲተገበሩ፣ ቴሌ ከንፌሬንስ ሴንተር ምክር ቤቱ እንዲኖረው እና የምክር ቤት የራሱ ቴሌቪዥን ማሰራጫ እንዲኖረው ስቱዲዮ በማስገንባትም ሆነ ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ከፍተኛ ጥረት ላይ እያሉ ለሌላ ተልዕኮ ከቦታቸው ተነስተዋል

የተከ. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጫናቃ
Education Level: - አንደኛ ደረጃ፤ ቢላቴ ጤና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ሁለተኛ ደረጃ፤ ሶዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ከፍተኛ ትምህርት ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስታስቲክስና ሥነ ሕዝብ የመጀመሪያ ዲግሪ - ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ አስተዳደርና የልማት ፖሊሲ ላይ ሰርተዋል
Experience

በክልል ደረጃ - በደቡብ ክልል ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ በተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል፡፡ በፌዴራል ደረጃ - ከመስከረም 30/1993 ዓ.ም ጀምሮ የወጣቶች፣ ስፖርትና ባህል ሚኒስትር - ከ1998 --- 2002 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ - ከ2003 --- 2007 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - ከሚያዚያ 11/2010 --- ጥቅምት 6/2011 የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር በአምባሳደርነት/እኤአ/ - ጋና፡- ከ1992 --- 1993 - ግብጽ፡- ከ1993 --- 1996 - ኬንያና ታንዛኒያ፡- ከ1996 --- 2001 - በፈረንሳይና - በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ከ2013 --- 2019 - በቻይና ከ2019 ጀምሮ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የአፈ ጉባኤነት ቆይታቸው - የደንብ ቁጥር 6/2008 መተግበሪያ የሚሆኑ 28 መመሪያዎች በማውጣት የምክር ቤቱ ስራዎች በዝርዝር ህጎች እንዲመሩ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል - ተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላት በብዛት ወደምክር ቤቱ በገቡበት ጊዜ የምክር ቤቱ መድረክ ፈታኝ በሆነበት ወቅት በጥበብ መድረኩን በመቆጣጠር ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል - የምክር ቤቱን ዋና ሕንጻ በማደስና ተገጣጣሚ ቤቶችን በመስራት ምክር ቤቱን ለሥራ ምቹ አድርገዋል - የጽ/ቤቱንም መዋቅር በማሻሻል የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ወደምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት የሚፈልሱበት መስሪያ ቤት እንዲሆንም አስችለው ነበር - የአባላትን ጥቅም በማስከበር በኩል በድክመት ከአቶ ዳዊት ዮሐንስ አይተናነሱም፡፡ ከምክር ቤት አባላት የመቋቋሚያ አበል ላይ 35 በመቶ ታክስ እንዲቆረጥ ሲወሰን አፈ ጉባኤው ዝምታን መርጠዋል፡፡

የተከ. ወ/ሮ ሎሚ በዶ ቁምቢ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ:- በቋንቋ ዲፕሎማ - በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ - በሊደርሽፕ ሁለተኛ ዲግሪ
Experience

የስራ ልምድ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዕርከኖች በአመራርነት በወረዳ ዋና አፈ ጉባኤነት በወረዳ ዋና አስተዳዳሪነት በክልል ደረጃ በተለያዩ ሃላፊነት ደረጃዎች ሲያገለግሉ ከነዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር የክልሉ የንግድ ቢሮ ሃላፊ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ በ1997 ምርጫ ተወዳድረው የዱግዳ መቂ ምርጫ ክልል ሕዝብን በመወከል ከ1998 – 2002 ዓ.ም ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ከምክር ቤት አባልነት በኋላም የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሕገ መንግስትና ማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ አባል የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ የዱግዳ መቂ ምርጫ ክልል ሕዝብን በመወከል ከመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና ምክትል አፈ ጉባኤ በመሆን

የተከ. ታገሰ ጫፎ ዱሎ
Education Level: የትምህርት ሁኔት - ከፍተኛ ትምህርት፡- በሥነ ህይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል - በዓሳ ሀብት ሳይንስና እርባታ ከህንድ አገር የማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል - በንግድ ስራ አስተዳደር ሌላ የማስተርስ ዲግሪ ሰርተዋል፡፡
Experience

የስራ ሁኔታ፡- በክልል ደረጃ - በደቡብ ክልል በወረዳ አመራርነት ለ2 ዓመት - በደቡብ ክልል በዞን አመራርነት ለ6 ዓመት - በደቡብ ክልል በኢንቨስትመንት ኮሚሽነርነት - በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ - በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ በፌዴራል ደረጃ - ከ2007 ዓ.ም --- ጥቅምት 22/2009 የኢፌዲሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሚኒስትር ዴኤታ - ከ2008 --- መስከረም 2014 ዓ.ም ድረስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - ከጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም --- መጋቢት 10/2010 ድረስ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር - ከመጋቢት 22 ቀን 2010 --- መስከረም 2014 ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ - ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና ከመስከረም 24 ቀን 2014 ጀምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

የፕሬዚዳንት አሰያየም

የፕሬዚዳንት አሰያየም ሂደቱ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ስለጠቅላይ ሚኒስትር አሰያየም የቀረበው ማብራሪያ በቂ ስለሆነ እዚህ መድገም አያስፈልግም፡፡ ህጉ እና የነበረው ተሞክሮ ምን እንደሚመስል በአጭሩ በማሳየት ጉዳዩ እንዲጠቃለል ይደረጋል፡፡
  1. ለኘሬዚዳንትነት እጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው
  2. የቀረበው እጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ኘሬዚዳንት ይሆናል፡፡
  3. የምክር ቤት አባል ኘሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን የምክር ቤት ወንበር ይለቃል፡፡
ስለፕሬዚዳንት አሰያየም ከሚደነግገው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 70 ስር እነዚህ ከላይ የተመለከቱ ሶስት ንዑሳን አንቀጾች ይገኛሉ፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የሚቀርብ ፕሬዚዳንት የሚሰየም ሳይሆን በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ 2/3 ድጋፍ ድምጽ የሚመረጥ መሆኑን ከንዑስ አንቀጽ 2 መገንዘብ ይቻላል፡፡
በምክር ቤቱ ያለው ልምድም ይህን ድንጋጌ የሚከተል ነው፡፡ የቀድሞ ፕሬዚዳንት / ነጋሶ ጊዳዳ 6 ዓመት የሥራ ጊዜያቸውን በሁለተኛው ምክር ቤት  1994 . በመስከረም  ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ባጠናቀቁበት ወቅት ሁለቱ ምክር ቤቶች ዕጩ ፕሬዚዳንት የሚመርጡበት የጋራ ስብሰባ ነበሯቸው፡፡
በአጀንዳው መሰረት ተረኛው አፈ ጉባኤ ዕጩ ፕሬዚዳንት እንዲቀርብ ዕድሉን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰጠ፡፡ በዚህ መሰረት በዕጩነት የተከበሩ ፕሮፌሴር በየነ ጴጥሮስ እና የተከበሩ መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቀረቡ፡፡ የተከበሩ መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቤቱን 2/3 ድጋፍ ድምጽ በማግኘት ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡፡ ህጉም ሆነ ልምዱ የሚያሳየው ፕሬዚዳንት የሚኮነው በምርጫ መሆኑን ነው፡፡ 
ስልጣንና ተግባሩ
  1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል፡፡
  2.  በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጃል፡፡
  3.   ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠ ቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል፡፡
  4.  የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል፡፡
  5.   በሕግ መሰረት ኒሻኖችና ሽልማቶችን ይሰጣል፡፡
  6.   በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል፡፡
  7.  በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡

የተከ. ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሶለን
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - ከፍተኛ ትምህርት፡- በታሪክ የዶክትሬት ዲግሪ ከጎቴ ዩኒቨርሲቲ፤ ፍራክፈርት፤ ጀርመን
Experience

የስራ ልምድ - 25/12/1993 --- 25/12/ 1984 ዓ.ም የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር - 26/12/1984 --- 18/12/1987 ዓ.ም ማስታወቂያ ሚኒስትር - 18/12/1987 --- 28/01/1994 ዓ.ም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት - 29/01/1994 --- 30/10/1997 ዓ.ም የቀድሞ ፕሬዚዳንት - 29/01/1998 --- 30/01/2003 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - የሁለት ፋብሪካዎች የስራ አመራር ቦርድ ሊቀ መንበርና የኩኒዝ ኮሌጅ አማካሪ ሆነውም ሰርተዋል

የተከ. ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሉጫ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - የቤተ ክህነት:- ከ1926 እስከ ጣሊያን ወረራ ድረስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት - ከ1930 እስከ 1933 የጣሊያኖች ትምህርት ቤት/ዘ ስኮላ ፕሪንሲፔ/ ዘመናዊ ትምህርት ተከታትለዋል - ከ1942 እስከ 1944 በዓለም አቀፍ የሲቪል ማህበር ድጋፍ በሚሰጠው የማሰልጠኛ መርሐ ግብር - ከሆላንድ አገር በአስተዳደር ሙያ - ከሲውዲን አገር በአየር ትራፊክ አስተዳደር - ከካናዳ አገር በአየር ትራፊክ መቆጣጠር የተለያዩ የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል
Experience

የስራ ልምድ - በ1933 በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች የሬዲዮ መገናኛ ክፍል ባልደረባ - በ1936 ከገነት ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የምክትል ሌፍተናንት ምሩቅ - በ1938 የኢትዮጵያን አየር ሃይል በመቀላቀል ልዩ ልዩ አስተዳደራዊ ኮርሶችን ተከታትለዋል - በ1940 በአየር መቃወሚያና በበረራ መቆጣጠሪያ ማዕከል ረዳት መምህር - በ1947 በኤርትራ የፌዴራል መንግስት የሲቪል አቢዬሽን የበላይ አዛዥ - በ1951 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዳይሬክተር - በ1953 የፓርላማ አባል - ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የፓርላማ ፕሬዚዳንት አይ ፒ ዩ በስዊዘርላንድ፣ በዴንማርክና በዩጎዝላቪያ ባደረጋቸው ኮንፌንሶች ኢትዮጵያ ተሳታፊ እንድትሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል - በ1952 አይ ፒ ዩ ስብሰባ ላይ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት - በ1967 የንግዱን ማህበረሰብ በሲቪል ኮንሰልቲቭ ኮሚሽን የውክልና አገልግሎት በአይ ኤም ፒኢ ኤክስ አስመጪና ላኪ - በ1969 በጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት የኤርትራን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በተቋቋመው የሰላም ኮሚሽነር ፕሮግራም ተቀዳሚ ኮሚሽነር - የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የቦርድ አባል - በኢትዮጵያ አውስትራሊያ ንግድ ልዑክ ወኪል - የጊቤ እርሻ ልማት ማህበር መስራችና ዳይሬክተር - የከፋ ቲምበር ፕሮሴሲንግ ኢንዱስትሪ መስራችና ዳይሬክተር - ከ1982 በፊት በኤርትራ አገር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ኤርትራ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት - የቼሻየር ሆም የቦርድ ፕሬዚዳንት - የሊፕሬዚ መቆጣጠሪያ ድርጅት ማነጅንግ ዳይሬክተር - በ1982 ከኤርትራ ሲመለሱ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የቦርድ ዳይሬክተርና በዚሁ መስሪያ ቤት በዓለም አቀፍ ሎጂስቲክ ዲፓርትመንት የበላይ ጠባቂ - በ1993 ለም ኢትዮጵያ በተሰኘውና በአካባቢ ጥበቃ ላይ በሚሰራው ማህበር የቦርድ ፕሬዚዳንት - በ1992 በተደረገው ሁለተኛው የምክር ቤት አባልነት ምርጫ በኦሮሚያ የበቾ የምርጫ ክልል ህዝብን በመወከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - ከመስከረም 28 ቀን 1994 --- መስከረም 28 ቀን 2000 ዓ.ም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት - ከመስከረም 28 ቀን 2000 ዓ.ም --- መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ከመስከረም 27 ቀን 2006 ጀምሮ የቀድሞ ፕሬዚዳንት

የተከ. ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ውርቱ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ፡- አርጆና አዲስ አበባ - ከፍተኛ ትምህርት ከቻይና ቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በፖለቲካል ኤኮኖሚ ፍልስፍና የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ከአሜሪካ ፍሌቼር የህግና ዲፕሎማሲ ትምህርት ቤት በ1980 ዓ.ም በህግና ዲፕሎማሲ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ ከቻይና ቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ በ1983 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ህግ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
Experience

የስራ ልምድ - ከ1987 – 1993 ዓ.ም በኤኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር - ከ1993 – 1994 ዓ.ም የግብርና ሚኒስትር - ከ1994 – 1998 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ - ከ1984 – 1986 ዓ.ም በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር - ከ1986 – 1987 ዓ.ም በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር - ከ1999 – 2006 ዓ.ም በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር - ከመስከረም 27 ቀን 2006 -- ሚያዚያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት - ከሚያዚያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞ ፕሬዚዳንት

የተከ. ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - አንደኛ ደረጃ ፡- ሊሴ ገብረ ማርያም - ሁለተኛ ደረጃ፡- ሊሴ ገብረ ማርያም - ከፍተኛ ትምህርት፡- ፈረንሳይ መንቴፔለ ዩኒቨርሲቲ/በተፈጥሮ ሳይንስ ዲግሪ/
Experience

የስራ ልምድ - በትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል - በትምህርት ሚነስቴር የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ - ለኢትዮጵያ እንደውጭ አገር አገልግሎት ሰራተኛ ሆነው ብዙ ዓመታትን አገልግለዋል - ከ1989 – 1993 ሴኔጋል ተቀማጭ ሆነው የማሊ፣ የኬፕበርድ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር - ከ1993 – 2002 በጅቡቲ አምባሳደርና በምስራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግስታት ቋሚ መልዕክተኛ - ከ2002 – 2006 በፈረንሳይ አምባሳደርና በተባበሩት መንግስታት የዩኔስኮ ተወካይ - በተባበሩት መንግስታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተወካይ በመሆን የማዕከላዊ አፍሪካ ሃላፊ በመሆን - በኤዩ እና በአፍሪካ ኤኮኖሚ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ በመሆን - በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል - በ2011 በኬንያ የዩ ኤን ዳይሬክተር ጀኔራል ሆነው በባን ኪሙን ተሸመዋል - በአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይና በኤዩ የዩኤን ቢሮ ሃላፊ ሆነው በጉቴሬዝ ተሸመዋል - ከሚያዚያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት - ‘’ጠንካራ ሴት’’ የሚል አድናቆት ያገኙና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊዎች ተደጋጋሚ ሹመቶች እያገኙ ሃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አሰያየም

የባለስልጣኖችን ሹመት ማፅደቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር አንዱ መሆኑን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ 13 ያመለክታል፡፡ በምክር ቤቱ ሹመታቸው ከሚፀድቁ ባለስልጣኖች መካከል የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት እንደሚገኙ በዚሁ ድንጋጌ ተገልጿል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትሮችና በህግ በሚወሰን መሰረት ሌሎች አባሎች የሚገኙበት እንደሆነ ደግሞ በአንቀፅ 76 ንዑስ አንቀፅ 1 ተዘርዝሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር በምክር ቤቱ የሚሰየመው እነዚህን የህግ አግባቦች ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 73 ጋር በማያያዝ ነው፡፡ አንቀፅ 73 ለጠቅላይ ሚኒስትር ስያሜ መሰረታዊ የሆኑ መመዘኛዎችን የሚይዝ ድንጋጌ ነው፡፡ አንዱ መመዘኛ በንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የሚሰየም ሰው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የመሆን ግዴታ ነው፡፡ በምክር ቤቱ አባልነት ያልተመረጠ ሰው ለዚህ ሃላፊነት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ በንዑስ አንቀፅ 2 የተቀጠው መመዘኛ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የሚሰየመው ሰው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ካገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ካገኙ ጣምራ  የፖለቲካ ድርጅቶች  ለሃላፊነቱ ውክልና ያገኘ መሆን አለበት፡፡ የነዚህ መመዘኛዎች መሟላት አንድን ሰው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ስያሜ ያበቃል፡፡
የህገ መንግስቱ አንቀፅ 73 ንዑስ አንቀፅ 1 ጠቅላይ ሚኒስትር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል እንደሚመረጥ ይደነግጋል፡፡ ይህ ‘’ይመረጣል’’ የሚለው ሐረግ ‘’መሰየም‘’ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡ የምርጫ ትርጉም ከስያሜ ይለያል፡፡ ምርጫ ማወዳደርን ያመለክታል፡፡ ስያሜ ከሆነ ለአንድ ተቋም ወይም ለአንድ ግለሰብ የተባለውን ሃላፊነት በቀጥታ መስጠትን ይመለከታል፡፡ 
ከዚህ ቀደም በነበሩ ልምዶች ለአንድ ምክር ቤት አባል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን የሚሰጠው በምርጫ እንጂ በስያሜ አስተሳሰብ አይደለም፡፡ በመጀመሪያው ምክር ቤት ነሐሴ 15 ቀን 1987 . መንግስት ሲመሰረት አቶ መለስ ዜናዊ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተጠቆሙ በሗላ አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሐንስ ከአቶ መለስ ጋር የሚወዳደር የምክር ቤት አባል እንዲጠቆም ዕድል የሰጡ ቢሆንም ሌላ ተወዳዳሪ ባለመገኘቱ መጀመሪያ የተጠቆሙት አባል በቀጥታ ማለፋቸውን ለመግለፅ ሲሉ የእንግሊዝኛውን acclamation የሚለውን ቃል መጠቀማቸውን ማስታወስ ስያሜው በምርጫ አስተሳሰብ ውስጥ ሆኖ ስለመከናወኑ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይ ችሏል፡፡
ለዚህ አባባል ጥሩ ማሳያ የሚሆነው 1993 . 2ኛው ምክር ቤት ሲመሰረት ጉባኤውን የመሩት አፈ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሰየም ያቀረቡት ሃሳብ ነው፡፡ ‘’… ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በዕጩነት ሊቀርቡ የሚችሉ ግለሰቦችን ጥቆማ ማቅረብ እንደሚቻል በክቡር አፈ ጉባኤው በተገለጸው መሰረት /ክቡር ዶር ካሱ ይላላ/… መለስ ዜናዊን በዕጩነት የጠቆሙ ሲሆን ጥቆማው 1/3 ድምጽ በላይ ድጋፍ ያገኘ በመሆኑ ተቀባይነትን አግኝቷል‘’ ይላል ቃለ ጉባኤው፡፡ በማስከተልም ‘’… ሌላ ጥቆማ ካለ እንዲቀርብ /ክቡር አፈ ጉባኤው/ ቢጠይቁም ባለመቅረቡ ምክር ቤቱ መለስ ዜናዊን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በቀጥታ በሙሉ ድምጽ መርጧቸዋል‘’ ይላል ይህ ቃለ ጉባኤ፡፡ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣንና ተግባር የሚደነግገው የህገ መንግስቱ አንቀፅ 74 ሲታይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ የሀገሪቱን የውጭ ፖሊሲ በበላይነት የሚያስፈፅም መሆናቸውን ደግሞ ከንዑስ አንቀፅ 6 መመልከት ይቻላል፡፡ ህገ መንግስቱን የማስከበር ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑንም ከንዑስ አንቀፅ 13 መገንዘብ ይቻላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሃላፊነት የሚሸከም የምክር ቤት አባል በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊሰየም ከሆነ አስቀድሞ ከሁሉም አባላት በአንፃራዊነት በብቃቱ ይሻላል የሚባል የምክር ቤት አባል ይቀርባል እንጂ ለምርጫ ሲባል የሚደረግ ስራ ተደርጎ ስያሜ ሊወሰድ አይገባም፡፡
ስያሜ ከድርጅት ጉባኤ ጋርም ይያያዛል፡፡ በምርጫ ማግስት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘው የፖለቲካ ድርጅት ጉባኤውን በማካሄድ አመራሩን ይመርጣል፡፡ አገር የሚመራበት ሁኔታ ላይም ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡ ይህ ጉባኤ የፖለቲካ ድርጅቱ የመጨረሻ የስልጣን አካል ነው፡፡ ይህ ጉባኤ የድርጅቱ ሰብሳቢ እንዲሆን የመረጠው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንደገና የምክር ቤቱ አባል ከሆኑ የራሱ ሰዎች ጋር ሊወዳደር አይገባም፡፡ በምክር ቤቱ ያሉት የፖለቲካ ድርጅቱ አባላት የድርጅቱን ሰብሳቢ በጉባኤው ሲመረጥ በአንፃራዊነት ከኛ የተሻለ ነው ብለው ይሁንታ የሰጡ ስለሆኑ እንደገና ሊወዳደሩት አይገባም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መንግስት የሚመራ ቢሆንም የፖለቲካ ድርጅቱን አቅጣጫ ተከትሎ የሚሰራ ስለሆነ የድርጅቱን አመራር ቦታ ያገኘ የምክር ቤቱ አባል በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ይሰየማል፡፡
በዚህ በኩል 6ኛው ምክር ቤት ‘’ጠቅላይ ሚኒስትር መሰየም’’ የሚለው ሐረግ በትክክል ተተርጉሟል፡፡ አፈ - ጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሰየም ዕድሉን በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ላገኘው የፖለቲካ ድርጅት ሰጡ፡፡ ከድርጅቱ ለዚህ ጉዳይ ሃላፊነት የወሰደው የምክር ቤቱ አባል የድርጅቱ ሰብሳቢ ሆኑትን የምክር ቤት አባል በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲሰየሙ ግለ ታሪካቸውን አቀረቡ፡፡ አፈ ጉባኤውም መግለጫውን ተከትለው ግለ ታሪካቸው የቀረበው የምክር ቤቱ አባል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን አወጁ፡፡ የምክር ቤቱ አባላትም እወጃውን በጭብጨባ ተቀበሉ፡፡ የተሰየመውም የምክር ቤት አባል ቃለ መሐላ ፈጸሙ፡፡ ዳግም ጭብጨባ ፡፡ መሰየም ማለት አስቀድሞ ለታወቀ አካል ሃላፊነት መስጠት መሆኑን መስከረም 24 ቀን 2014 . ጠዋት በምክር ቤቱ ጉባኤ አዳራሽ የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰየም ተግባር ትክክለኛ አሰራሩንና አስተሳሰቡን አሳይቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መልክ ከተሰየሙ በሗላ በአንቀፅ 74 የተደነገጉትን ስልጣንና ተግባር መፈፀም ይጀምራል፡፡
ስልጣንና ተግባሩ
አንቀጽ 74 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር
  1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው፡፡
  2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያጸድቃል፡፡
  3. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጐች፣ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
  4. የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይወክላል፡፡
  5. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣቸውን ፖሊሲዎች፣ ደንቦች መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ይከተተላል፡፡
  6. የሀገሪቱን የውጭ ፖሊሲ በበላይነት ያስፈጽማል፡፡
  7. ኮሚሽነሮችን፣ የማዕከላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንትን እና ዋና ኦዲተርን መርጦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያጸድቃል፡፡
  8. የመስተዳድሩን ሥራ አፈጻጸምና ብኝት ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ የሆኑ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡
  9. በዚሀ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 7 ከተዘረዘሩት ውጭ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሲቪል ሹመቶችን ይሰጣል፡፡
  10. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ሕግ ወይም በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ለኘሬዚዳንቱ አቅርቦ ያሰጣል፡፡
  11.  ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ፣ በመንግሥት ስለተከናወኑ ተግባራትና ስለወደፊት እቅዶች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ ሪፖረት ያቀርባል፡፡
  12. በዚህ ሕገ መንግሥትና በሌሎች ሕጐች የተሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፡፡
  13. ሕገ መንግሥቱን ያከብራል፤ የስከበራል፡፡

የተከ. አቶ መለስ ዜናዊ አስረስ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - አንደኛ ደረጃ፡- እስከ 8ኛ ክፍል አድዋ ንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት - ሁለተኛ ደረጃ፡- ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል በአዲስ አበባ ጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት/1961 – 1964/ -ከፍተኛ ትምህርት፡- ከ1965 – 1967 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፋኩልቲ የህክምና ትምህርት - እኤአ በ1995 ከዩናይትድ ኪንግደም ኦፕን ዩኑቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ - እኤአ በ2004 ከኔዘርላንድ አራስመስ ዩኒቨርሲቲ በኤኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ
Experience

የስራ ልምድ - በ1983 ግንቦት 20 አዲስ አበባን ኢህአዴግ ከተቆጣጠረ በኋላ ለአንድ ወር የኢህአዴግ ጊዛዊ መንግስት ፕሬዚዳንት - ከሐምሌ ወር 1983 --- ነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት - ከነሐሴ 15 ቀን 1987 -- ነሐሴ 2004 ዓ.ም ድረስ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል • የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና ዋና አመንጪ • ለ42 ዓመታት የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ • ተደማጭና ተጽዕኖ ፈጣሪ • የሕዳሴ ግድብ መሐንዲስ • አባይን የደፈረ ጀግና • ከአየር ንብረትና ለውጥ ጋር በተያያዘ በቡድን 8 እና በቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ድምጽ በማስተጋባት ‘የአፍሪካ ቃል አቀባይ’ የሚል ስም ያገኙ

የተከ. አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ
Education Level: የትምህርት ሁኔታ - አንደኛ ደረጃ፡- አየርላንድ ካቶሊክ ሚሽን - ሁለተኛ ደረጃ፡- ወላይታ ሶዶ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ከፍተኛ ትምህርት • ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1980 በኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ • ከፊንላንድ ተምፔሬ ዩኒቨርሲቲ በሳንቴሽን ምህንድስና የማስተርስ ዲግሪ • ከአሜሪካው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በድርጅት አመራር የማስተርስ ዲግሪ
Experience

የስራ ልምድ - እንደተመረቁ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት መምህር - ከማስተርስ በኋላ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ዲን /ለ13 ዓመታት/ - የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት - ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ለ4 ዓመታት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ፕሬዚዳንት - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ - የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል- አቶ ክፍሌ ጃጉባ ታኮሬ የተባሉ የቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል ተወካይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በግል ፍላጎታቸው ምክር ቤቱን በመልቀቃቸው ምክንያት ክቡር አቶ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ በምትካቸው በማሟያ ምርጫ በ2001 የምክር ቤቱ አባል ለመሆን ችለዋል - ከጥቅምት 20/2001 -- ከመስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር - ከመስከረም 25 ቀን 2003 -- መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - ነሐሴ 14 ቀን 2004 -- መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር - ከመስከረም 11 ቀን 2005 -- መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር - የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ - መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር • የመለስ ሌጋሲ አስቀጣይ • ለለውጥና ለሰላም ሲሉ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣንን በመልቀቅ ፋና ወጊ ሆኑ ኢትዮጵያዊ • ትክክለኛ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በዚህ አገር ላይ እንዲተገበር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ መሪ

የተከ. ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ
Education Level: - ከፍተኛ ትምህርት • በ1994 ዓ.ም ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ • በ1997 ከደቡብ አፍሪካ በክሪፕቶግራፊ አድቫንሲድ ዲፕሎማ • በ2003 ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ሎንደን ማስተርስ ዲግሪ በሊደርሺፕ እና ለውጥ • አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ ከሊድ ስታር ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በሚሰጠው ድህረ ምረቃ ፕሮግራም በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስተርስ ዲግሪ/MBA/ • ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት 3ኛ ዲግሪ/ፒኤችዲ/ ‘’ሀገር በቀል ግጭት አፈታት የማህበራዊ ሀብት ሚና’’ በሚል ርዕስ መመረቂያ ጽሑፍ በማቅረብ አግኝተዋል
Experience

የስራ ልምድ - በመከላከያ ሚኒስቴር ከተራ ወታደር እስከ ሌተናል ኮለኔል ማዕረግ - በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሃላፊና የኤኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ - በኢፌዲሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል እና የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራችና አመራር - ኢፌዲሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር - ከ2003 ዓ.ም --- 2008 ዓ.ም የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - ከ2008 ዓ.ም --- 2014 ኣ.ም የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል - በበርካታ የሥራ ሃላፊነት ቦታዎችና በቦርድ ውስጥ የሰሩ - ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር • አቃፊና ትዕግስተኛ መሪ • አገር ወዳድና ግንባር ቀደም መሪ • የልማት አርበኛ • ጥቅምነታቸው ያልታወቁ ሀብቶችን አውቀው ወደጥቅም በመለወጥ የታወቁ • የኢትዮጵያን መፃኢ ዕጣ - ፈንታ የሚወስኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ወደተግባር ያሸጋገሩ

የፓርቲ ተጠሪዎች አሰያየም

   ከላይ የተመለከቱት መሰየሞች መሰረታቸው የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ሲሆን የፓርቲ ተጠሪዎች አሰያየም መሰረታቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ደንብ የሚወያጣው ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 የወጣውም ‘’ምክር ቤቱ ስለ አሠራሩና ስለ ሕግ አወጣጡ ሂደት ደንቦችን ያወጣል’’ የሚለውን የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 2 ተከትሎ ነው፡፡

የዚህ ደንብ አንቀጽ 204 እና 208 ስለፓርቲ ተጠሪዎች አሰያየም የሚደነግጉ ሲሆን አንቀጽ 204 ‘’የመንግስት ዋና ተጠሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ‘’ እና ‘’ረዳቶቹ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዋናው የመንግስት ተጠሪ ጋር በመመካከር‘’ እንደሚሰይሙ ያመለክታል፡፡ በድንጋጌው መሰረት ብቸኛው የስልጣኑ ባለቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው ፡፡ በሌላ አነጋገር በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ መሆኑን ድንጋጌው ያሳያል፡፡

 አንቀጽ 208 የፓርቲ ተጠሪዎች ‘’በምክር ቤቱ ባሉ አባሎቻቸው ወይም በፓርቲ መሪዎቻቸው‘’ እንደሚሰየሙ ይደነግጋል፡፡ የመሰየሙ ጉዳይ ብቸኛ ባለመብት በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር ከያዘው የፖለቲካ ፓርቲ ቀጥለው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ናቸው፡፡ 

  • የመንግስትና የፓርቲ ተጠሪዎች ስልጣንና ተግባር
  • አባሎቻቸው ስለምክር ቤቱ አጀንዳዎች አስቀድመው እንዲያዉቁ ያደርጋሉ፤
  • አባሎቻቸው በምክር ቤቱ ስብሰባዎች እንዲገኙ እና ለፓርቲያቸው ድምጽ እንዲሰጡ ያደርጋሉ፤
  • በምክር ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የፓርቲያቸው አባላት ለሥራቸው ብቁና ዝግጁ ሆነው እንዲገኙ ቀጣይነት ያለው ሥራ ይሠራሉ፤
  • ፓርቲያቸውን በመወከል ለምክር ቤቱ የተለያዩ ኮሚቴዎች የሚሳተፉ ወይም ለሌሎች ተልዕኮዎች የሚያስፈልጉ አባሎቻቸውን ዝርዝር ለሚመለከተው አካል ያቀርባሉ፡፡
  • ምክር ቤቱ ውስጥ በፓርቲ ተጠሪነት ያገለገሉ ባለስልጣናት

ይህ አደረጃጀት ህጋዊ ሆኖ የመጣው ምርጭ 97 ተከትሎ ነው፡፡ በሁለተኛው ምክር ቤት በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የደቡብ ኅብረት በምክር ቤቱ 10 ያላነሰ መቀመጫ በመያዝ በምክር ቤቱ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲያድግ መንገድ የከፈተ ሲሆን 1997 ምርጫ ደግሞ ያልተጠበቀ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕድገት በምክር ቤቱ እንዲመዘገብ የራሱን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡

1997 ምርጫ የምክር ቤቱን መቀመጫ ያገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ቁጥር ወደ180 ያህል እንደሆነ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገለጸ ቢሆንም ከኋላ በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የአባላቱ ቁጥር ወደ140 እንዲወርድና አንዳንድ ፓርቲዎችም ምክር ቤቱ ከመግባት ራሳቸውን እንዲያገልሉ አድርጓቸዋል፡፡

ከነችግሩም ቢሆን ወደምክር ቤቱ የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማስተናገድ ይህ አደረጃጀት ተፈጥሯል፡፡ አደረጃጀቱም የምክር ቤቱን ስራዎች ፓርቲን መሰረት አድርጎ እንዲከናወኑ ለማስቻል ነው፡፡ የደንቡ አንቀጽ 202 ስለዚህ ጉዳይ ሲገልጽ ‘’ምክር ቤቱ ስራውን በተደራጀና በተገቢው መንገድ ለመወጣት እንዲያስችለው‘’ በማለት ነው፡፡

የመንግስት ዋና ተጠሪ

የፖለቲካ ድርጅት

የስራ ጊዜ

የመንግስት ረዳት ተጠሪ

የፖለቲካ ድርጅት

የስራ ጊዜ

 

የተከበሩ አቶ ሽፈራው ጃርሶ

   

 ኦህዴድ

 

ከጥቅምት 1998 -- ጥቅምት 20/2001 ዓ.ም

የተከበሩ ወ/ሮ ነጻነት አስፋው

ሕወሓት

ከጥቅምት 15 ቀን 1998  መስከረም 24 ቀን 2003 ዓ.ም

የተከበሩ ወ/ሮ ሮማን ገብረሥላሤ

ሕወሓት

ከጥቅምት 8 ቀን 2003 ዓ.ም -- ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም

 

የተከበሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

 

ደኢህዴን

ከጥቅምት 20/2001-- መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ  አጽብሃ አረጋዊ  

ሕወሓት

ከህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም -- ህዳር 22/2011 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ ገብረእግዚአብሔር አርአያ  

ሕወሓት

ከህዳር 22/2011 --- መስከረም 25 ቀን 2013

 

የተከበሩ / አስቴር ማሞ

   

ኦህዴድ

መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም --- ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ ጌታቸው በዳኔ

ኦህዴድ

ከጥቅምት 15 ቀን 1998 -- ህዳር 22/2011 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ ጫላ አርገኔ

ኦህዴዴ

ከህዳር 22/2011 --- መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

 

የተከበሩ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

 

ሕወሓት

ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም --- መስከረም 25 ቀን 2008 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ መለስ ጥላሁን

ብአዴን

ከጥቅምት 15 ቀን 1998 -- ህዳር 22/2011 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ ጫኔ ሽመካ

ብአዴን

ከህዳር 22/2011 --- መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

 

 

 

 

የተከበሩ / ሮማን ገብረስላሴ 

 

 

 

 

 

ሕወሓት

 

 

 

 

መስከረም 25 ቀን 2008 ዓ.ም --መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም

 

 

የተከበሩ አቶ  ወንድሙ ገዛህን  

ደኢህዴን

ከጥቅምት 15 ቀን 1998 -- ጥቅምት 19/2006 ዓ.ም 

የተከበሩ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

ደኢህዴን

ከጥቅምት 19/2006 ዓ.ም -- 2008 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ አማኑኤል አብርሃም

ደኢህዴን

ከ2008 - ጥቅምት 27/2011 ዓ.ም

የተከበሩ አምባሳደር መስፍን ቸርነት

ደኢህዴን

ከጥቅምት 27/2011 ዓ.ም - መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

አቶ አብዱራሂም ያሲን ናስር

አጋር

ከጥቅምት 2008 - መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ አቶ ሀሰንአብዲ ጃማ

አጋር

ከጥቅምት 2008 - መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ በሺር  አሊ

አጋር

ከጥቅምት 2008 - መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

የተከበሩ አቶ ሹክሪ መዓሊን

አጋር

ከጥቅምት 2008 - መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም 

 

የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

 

ብልጽግና

 

ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ

የተከበሩ ረዳት ፕ/ር ምህረቱ ሻንቆ

ብልጽግና

 

ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ

ከበሩ ወ/ሮ መሠረት ኃይሌ

ብልጽግና