"በትምህርት ስርዓቱ የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" -- የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (/)

----------------

(ዜና ፓርላማ) ሚያዚያ 07 2017 .ም፤ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4 ዓመት የስራ ዘመኑ 24 መደበኛ ጉባዔው የትምህርት ሚኒስቴርን 2017 በጀት ዓመት 9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የሚንስቴር መስርያ ቤታቸውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት የሪፎርም ስራዎችን ለማሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላትንና የማህበረሰቡን ድጋፍ እንደሚጠይቅ አብራርተዋል፡፡

የትምህርት ሚንስቴር ቀጣዩ ትውልድ እውቀት ያለው፣ ብቁና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል በቁርጠኝነት በመስራት ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የመምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎችም የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።

12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ሪፖርቱን ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (/) ለሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አጠቃላይ ግብረ መልስ አቅርበዋል፡፡

የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ሪፎርም፣ የመምህርን እና የትምህርት አመራሮች ስልጠና እንዲሁም የተማሪዎች ምገባ ወጥ በሆነ መልኩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትምህርት ቤቶች የኮሚፒውተር፣ መብራት፣ መንገድ፣ ንጹህ ውሃ እንዲሁም ለዘርፉ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ማሟላት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

የመምህራን እጥረትን ለማቃለል የተቋረጠውን የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ማስቀጠል አንዱ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡  

የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አሰጣጥ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች ምደባ የህግ ማዕቀፍ ሊኖረው እንደሚገባ የተከበሩ ነገሪ (/) አሳስበዋል፡፡