(ዜና ፓርላማ) ጥር 8 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር መሐመድ ጋሊባፍ የሚመራውን ልዐካን ቡድንን በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።
የተከበሩ አቶ ታገሰ ኢትዮጵያና ኢራን ተመሳሳይ ባህልና ሀይማኖት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት መሆናቸውን ገልፀዋል።
የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በቀጣይም መጠናከር እንዳለበት የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናግረዋል።
የኢራንን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር መሐመድ ጋሊባፍ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።
በኢራንን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር መሐመድ ጋሊባፍ የሚመራው ልዑካን ቡድን በቀጣይም በምክር ቤቱ በመገኘት ሰፊ ውይይት እና የተለያዩ ጉብኝቶችን እንደሚያደርግም ይጠበቃል።