የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null The elected women CAUCUS members noticed that attention should be by given to the current national issues.

በአገሪቱ ባለው ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት ገለጹ፡፡

መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት የ2011 በጀት አመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የኮከሱ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ከም/ቤቱ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን የመላዋን ሴት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተደራጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡  

ይህን ዓላማ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ከክልሎችና በከተማ አስተዳደር እስከ ቀበሌ ም/ቤት ድረስ የተመራጭ ሴቶች ኮከስ ተደራጅተው ሴቶችን በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ ዘርፍ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና እኩል ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ በግንባር ቀደምነት እየሰሩ በመሆናቸው በራሳቸውና በሌሎች ሴቶች ላይ አንፃራዊ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት የኮከሱ አመራርና አባላት አቅም ተገንብቶ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ህግ የማውጣት፣ የቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም የህዝብ ውክልና ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ለም/ቤት በሚቀርቡና በተመረጡ አዋጆችና ሪፖርቶች ላይ በጋራ በመወያየት የሴቶችን እኩል ተሳታፊነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አጠቃላይ የኮከሱ እንቅስቃሴ ጥሩ መሆኑን ገልጸው፤ ወቅታዊ ጉዳይን በሚመለከት የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡  

ከነዚህም ውስጥ ከወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሴቶችና ህጻናት ተጎጂ በመሆናቸው እነሱን በሚመለከት ከመንግስት ጋር በመነጋገር የበኩላችንን ማድረግ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበርና በየቦታው የሚታየው መፈናቀል እንዲቆም የራሳችንን ጫና መፍጠር አለብን፣ ችግሮቹ ዘላቂ መፍትሄ እስከሚያገኙ ድረስም ድምጻችንን ማሰማት እና አፈናቃዩም አካል በህግ ሊጠየቅ ይገባል የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው በኮከሱ በኩል የተሰሩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውንና አሁን ባለው ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን መባሉ ጥሩ መሆኑ አንስተው ምክር ቤቱም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ከኮከሱ አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮከሱ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝና ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡