የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null The March 8 day ceremonies were celebrate in the House.

የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች  ቀን በህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት በድምቀት ተከበረ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበዓሉ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት የዘንድሮው ማርች 8 “”የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል  በአለም አቀፍ ደረጃ  ለ108ኛና  በኢትዮጵያ ለ43ኛ ጊዜ  መከበሩን አስታውሰው በአለማችን፣ በአህጉራችንና በአገራችን በነበሩ በርካታ ምክንያቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነተ ዝቅተኛ ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በሴቶች ላይ ለዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየው ጭቆና፣ የመብት ረገጣና አድሎዓዊ አሰራር እንዲወገድና በእኩልነት እንዲተካ እራሳቸው ሴቶች በግንባር ቀደምትነትና ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ባካሄዱት እልህ አስጨራሽ ትግል በተለያዩ ስምምነቶችና ዓለም ድንጋጌዎች እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ አገራቱም የየራሳቸው ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ የህግ አካል አድርገው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡

የአገራችንም ሴቶች የጭቆና ስርዓቶች በደል ገፈት ቀማሾች ሆነው እንደቆዩና የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና የማህበረሰቡ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተጠቂ በመሆናቸው ሴቶች የድርብ ጭቆና ተሸካሚዎች እንደነበሩ ጠቅሰው የአገራችን ሴቶች ጭቆናውን ለማስወገድ ከከፈሉት መስዕዋትነት ባሻገር ዛሬም በአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና አስተማማኝ ስላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል ምክትል አፈጉባዔዋ፡፡

ሴቶች በሴትነታቸው አድልዎ እንዳይደርስባቸው፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ፣ የሃይል ጥቃቶች ስጋት እንዳይሆንባቸው በህግ ማእቀፎች፣ በአሰራርና በግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የተደረገ እንቅስቃሴ እምርታዊ ለውጥ እንዳስመዘገቡ ተናግረው የተገኘውን ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥ ወንዶች አጋሮቻቸውን የለውጥ ሀይል በማድረግ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ልብ ማለት ይገባል ብለዋል ምክትል አፈ-ጉባኤዋ፡፡

ምክትል አፈ-ጉባዔዋ አክለውም በአሉም በአገራችን ለ43ኛ ጊዜ “የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል ሴቶች በተጎናጸፏቸው ዘላቂ የድል ቱርፋቶች ታጂቦና ደምቆ በመላ አገሪቱ ሲከበር ከመፈከር ባሻገር በተግባር በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማነኛወንም ጥቃት በደል ማስቆም፣ የኢኮኖሚ አቅማቸውን በመገንባት ልማትን ማፋጠንና የድህነትን እድሜ ማሳጠር መሆኑን በመገንዘብ ሴቶች በአገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ሀገራችን የተጀመረውን ተስፋ ሰጭ ለውጥ ከዳር ለማድረስ ቁርጠኝነት የምናሳይበት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻ ወ/ሮ ሽታየ እለቱ ሴቶች ለእኩልነት ያደረጉትን ትግልና የተገኙትን ውጤቶች የምንዘክርበትና ቀጣይነት በማረጋገጥ የሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን በተግባር ለማሳየት ቃል የምንገባበት፣ በቀጣይ ሰዎራዎቻችን ሁሉ በኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነት፣ መፈቃቀርና ይቅርታ እንዲሆን በአንክሮ የምንሰራበት ሊሆን ይገባል ሲሉ   መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የበዓሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ትምህርት ያላገኙ ሴት እህቶቻችን ስላሉ ትኩረት ተሰጥቶት በሰለጠነ ባለሙያ መሰራት እንዳለበትና ስለ ሰላም የሚሰብኩና የሚዘምሩ እናት አምባሳደሮች ስላሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተው በተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በዛፍ ስር ተጠልለው የሚወልዱ  እናቶች ስላሉ ችግሩን  ለመቅረፍ ልዩ ትኩረት አድርገን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡