null At Somali Regional State there is not set to develop and promote tourist attraction sites in citi zone.

በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሲቲ ዞን የሚገኙትን የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች በአግባቡ የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ አለመሰራቱ ተገለፀ፡፡

ግንቦት 12 ቀን 2011 .. ይህ የተጠቆመው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች /ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ በሲቲ ዞን አይሻ ወረዳ ያለውን የኢሳ ተራራ እና በኤረር ወረዳ የሚገኘውን የቀድሞ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቤተመንግስትና ፍል ውሀ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች እንዲሁም በሆቴሎች ላይ ባደረገው የመስክ ምልከታ ወቅት ነው፡፡

በምልከታው የአይሻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኑር ሀሰን በወረዳው የሚገኘው ታሪካዊ ተራራ በአካባቢው በብዛት ይኖር የነበረው የኢሳ ጎሳ 365 አንቀጾች ያለውን የጎሳው መተዳደሪያ ሕግ የወጣበትና 16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ታሪካዊ ቦታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቦታውም በወቅቱ የነበሩ መሪዎች የራሳቸው መለያ ምልክቶች በድንጋዮች ላይ ተጽፈው እንደሚገኙና ቅርሱንም በዩኔስኮ ለማስመዝገብ መታሰቡንም አብራርተዋል፡፡

በኤረር ወረዳ የሚገኘውን የቀድሞ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቤተመንግስትና ፍል ውሀ የቱሪስት መስህብ ቦታን በሚመለከትም ቦታው ለቱሪስት መስህብነት እንዲውል በሚል የተወሰነ እድሳት ቢደረግለትም ባለመጠናቁ ወደስራ አለመግባቱን፣ በቀጣዩ በጀት ኣመት ግን ተገቢውን በጀት በማስመደብ ታድሶ ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ የወረዳዋ የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ / ፈቲያ አህመድ በሰጡት ግብረ መልስ ወረዳው ከክልል መንግስት ጋር በመተባበር የቀድሞ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቤተመንግስትና ፍል ውሀ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራን ለማደስ የተደረገውን ጥረት በጥንካሬ አንስተው፣ በሁለቱም ወረዳዎች በሚገኙት የቱሪስት መስህብ ቦታዎች በአግባቡ አለመልማታቸው፣ ወደመዳረሻዎቹ የሚወስዱ መንገዶች እና ስፍራዎቹን የማስተዋወቅ ስራ ያለመሰራቱን በክፍተት አንስተዋል፡፡

በቀጣይ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎቹን አልምቶ ወደተግባር በማስገባትና በማስተዋወቅ ወደገቢ ምንጭነት መለወጥ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

በተመሳሳይም ቋሚ ኮሚቴው በሆቴሎች ላይ ባደረገው ምልከታ በዘረፉ የሰለጠኑ ባለሙዎች እጥረት መኖሩንና ሰራተኞቹም በሰራተኛ ማህበር አለመደራጀታቸውንም ታዝቧል፡፡

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤልያስ አቢብ መሀመድ በበኩላቸው ለቱሪስት መስህብ ቦታዎች የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር አምነው በቀጣይ ለዘርፉ ተገቢው ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡