null Attention is needed to build a strong and effective parliament.

ጠንካራና ውጤታማ ፓርላማን ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

ጥቅምት 18 ቀን 2012 በኢትዮጵያ ጠንካራና ውጤታማ የፓርላማ ሥርዓትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተወቀ፡፡

የኢ... የህዝብ ተወካዮች /ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ፓርላማው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በዋናነት ለህብረተሰቡ ጠቃሚና ምቹ የሆኑ ህጎችን የማውጣት፣ የአስፈጻሚ /ቤቶችን  መከታተልና  መቆጣጠር እነዲሁም የህዝብ ውክልና ስራዎችን በተገቢው መንገድ ለመፈፀም የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ አፈ- ጉባኤ ታገሠ ለልኡካኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፓርላማ ከባለፈው  አመት ጀምሮ ለስራው ማነቆ የሆኑ ህጎችን ያሻሻለ ሲሆን ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማትም እንዲኖሩ ሃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር  የፓርላማውን አሠራር ለማዘመን  በተለይ ደግሞ  የጽ/ቤቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተብራርቷል፡፡

በቶማስ ቶቤ የሚመራው አውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት  ከኢትዮጵያ ፓርላማ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት እዳለውና በተለይ በሰብዓዊ መብት አያያዝ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው ለውጥን ተከትሎ ግንኙነቱን ከበፊቱ የበለጠ ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ ለመነጋገር መምጣታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትም በአገሪቱ 110 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንዳለ ሁሉ በፓርላማው በርካታ መቀመጫ  እደሚኖር አንስተው የውክልና ስራ እና የአስፈጻሚ መስሪያቤቶችን የመከታተል፣ የመደገፍና የመቆጣጠሩ ሥራው ምን እንደሚመስል ጠይቀዋል፡፡

አፈ-ጉባዔውም  ፓርላማው በተቀመጠው የጊዜ እና የጥራት ደረጃ የክትትልና የቁጥጥር ስራ በስፋት እንደሚሰራ አንስተው በዓመት ሁለት ጊዜ የህዝብ ውክለና ያላቸው የፓርላማው አባላት ወደ ተመረጡበት የምርጫ ክልል በመሄድ የመስክ ምልከታ በማድረግ እና ከመራጩ ህብረተሰብ ጋር ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ነው፡፡

በቀጣይ የሚኖረው ምርጫን በተመለከተ  የልኡካን ቡድኑ የጠየቁ ሲሆን  አፈ-ጉባዔው 2012 ምርጫም ነጻ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ፓርላማው የምርጫ ህግ ከማሻሻል ጀምሮ የበኩሉን እየተወጣ እንደሆነና በተለይ አሁን በተፈጠረው ሰፊ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ተጠቅመው ፓርላማውን የሚቀላቀሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚኖሩ ተስፋ በማድረግ ፓርላማውም አድማሱን ለማስፋት እየሰራ እንደሆነ ነው፡፡

የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው በውይይቱ ወቅት አገራዊ ለውጥ ካመጣቸው ጥሩ ሂደቶች መካከል የደህንነትና መሰል የመንግስት ተቋማት አሠራራቸው እና ተጠያቂነታቸው  ግልጽ እንዲሆኑና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ዕድል ያመቻቸ  መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡ 

በመጨረሻም አውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት አሁን እየመጣ ባለው ለውጥ ላይ ድጋፋቸው እንደማይለይና ቀጣይ በሚደረገው ምርጫ ነጻና ፍትሐዊ እንደሆን በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ ሆነ በሌሎች ጉዳዮች  በጋራ እደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡