null Committee of the House evaluated 2019 budget 11 months performance report of the Ethiopian News Agency.

በህዝብ ተወካዮች ምር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የ2011 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ ሙለታ የመ/ቤቱን የ11 ወራት ዕቅድ ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡ ሲሆን መ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን፣ በዋና ዋና ተግባራት በአገሪቱ የዜና ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት፣ በመ/ቤቱ የሰራተኛን አቅም ለማጎልበት፣ ለሌሎች ሚዲያዎች የዜና ምንጭ በመሆን ተመራጭ ለማድረግ አቅደው ሲሰሩ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

አክለውም በ11 ወራት 12 ሺህ ዜናዎችን ለመዘገብ ከታቀደው በላይ በመስራት ከ13 ሺህ በላይ ተሰርቶ ለስርጭት መብቃቱን ገልጸው ዜናዎችን ለሌሎች ሚዲያዎች በመሸጥ ከ600 ሺህ ብር በላይ ገቢ እንደተገኘና ባጠቃላይ ዜናና ዜና ነክ ከሆኑት 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደተገኘም ነው የጠቆሙት፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ አቅሙን ለማጠናከር የአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች በመስጠት የአቅም ግንባታ ስራ መስራቱን ለአብነትም የግጭት ወቅት ዘገባና የልማታዊ ጋዜጠኝነት መርሆች ላይ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ሀሰተኛ እና አሳሳች ዜናዎችን ከትክክለኛ ዜና እንዴት መለየት እንደሚቻልም ጭምር መሆኑ በጠንካራ ጎን ገምግሟል፡፡

አሁን ላይ በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸው እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በጥናት በመለየት በተሰራው በተለይ በሰላም እና የማረጋጋት ጉዳዮች፣ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን በተመለከተ፣ የአገራችን የውጭ ግንኙነትና ተፈናቃይ ጉዳዮችን በመዘገብ የፖለቲካ ምህዳር መስፋፋት ላይ የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን በጥንካሬ ተነስቷል፡፡

በሌላ በኩል ተቋሙ ድህነት ቅነሳ ላይ ትኩረት በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎችና በክልል ከተሞች የተለያዩ  ጥናቶን መሰረት አድርጎ ለተቋማት ችግር ፈቺ የሚሆኑ ምክረ ሃሳቦችን የመጠቆም ስራ በስፋት ቢሰራም የጥናቱ ውጤት እና ያመጣው ለውጥ አለመገምገሙ በእጥረት ተገምግሟል፡፡

ከዚህ በፊት ሚዲያዎች የኢ.ዜ.አ ዜናዎችን ያለ እውቅና ወስደው የራስ የማድረግ ሁኔታ በመኖሩ አሁን ላይ ችግሩን ለመቅረፍ ከተለያዩ ሚዲያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ ቢደረስም በቅርንጫፍ ማዕከላት የተሰሩ ስራዎች አሁንም ሌሎች የራስ የማድረግ ሁኔታ እንዳለም የተቋሙ ኃላፊዎች ጠቁመዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አክሎ ተቋሙ ሌሎች ሚዲያዎች ተደራሽ በማይሆኑ ቦታዎች ላይ ገብቶ የሚሰራ እንደመሆኑ መጠን የቅርንጫፍ ማዕከላት ትኩረት መስጠትና አሁን ላይ የሚታየውን የግብዓት እጥረት መፍታ እንዳለበት ቢያነሳም የተቋሙ ኃላፊዎች የግብዓት እጥረት መንስኤ ከማዕቀፍ ግዢ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመው፣ የሰራተኞች ፍልሰትም ለስራው ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ ነው በማብራሪያው የተናገሩት፡፡