null Committee of the House evaluated 2019 budget 9 months performance report of the Ethiopian Electorioal Board.

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሰራሩን በማዘመን ምርጫውን ዲሞክራሲዊ፣ፍትሃዊ እና ተአማኒ ለማድረግ ማሻሻያዎች ላይ እየሰራን ነው ሲሉ የቦርዱ ሰብሳቢ /ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ አስታወቁ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን 9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን አስመልክቶ በርካታ ጥያቄዎችን አነስቷል፤ በህጋዊነት ያልተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ ግዴታቸውን ጠብቀው እንዲመዘገቡ ለማድረግ ቦርዱ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝቧል፤ 2011 የሚካሄደውን የአከባቢ /ቤት፣ የከተማ አስተዳደር የማሟያ ምርጫ ነጻ፣ዲሞክራሲያዊ፣ፍትሃዊ እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ ሆኖ እንዲካሄድ የሚስችሉ የዝግጅት ስራዎች እተሰሩ መሆናቸው ታውቋል ፡፡

የኢትዮጵ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ /ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ እንዳሉትም ቦርዱ አሰራሩን በማዘመን ምርጫውን ዲሞክራሲዊ፣ፍትሃዊ እና ተአማኒ ለማድረግ ማሻሻያዎች ላይ እየሰራን ነው ብለዋል ፡፡ አክለውም የቦርዱ አባላት ሙሉ በሙሉ ባለመሰየማቸው እና ወደ ስራ ባለመግባታቸው ለስራችን እንቅፋት ሆኖናል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ቦርዱ በተለያዩ ርእሶች ዙርያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ስልጠና መስጠቱን እና የምርጫ ስራውን ለማዘመን የሚስችሉ ማንዋሎችን በማዘጋጀት ስራ መስራቱን በጥንካሬ አንስቷል፤ ህብረተሰቡ በምርጫው ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን በምርጫ ህጎች እና አሰራሮች ዙሪያ ያለውን እውቀት ለማዳበር የስነ ዜጋና የመራጮች ግንዛቤ ማጎልበት ስራ ዝቅተኛ እና ቀጣይነት የሌለው መሆኑን በእጥረት ተመልክቶታል ቋሚ ኮሚቴው፡፡በሌላ በኩል ቦርዱ እጅግ ዘመናዊ እና ውድ የህትመት ማሽኖች ያሉት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ህግ ማሻሻያ ስርአትን አስመልክቶም ከወዲሁ ስራዎች ተጠናቀው ወደ ስራ መገባት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡