null Committee of the House evaluated 2019 budget 9 months performance report of the Ministry of Economy.

የገቢዎች፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚንስተርን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

በየጊዜው እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ግሽበት፣ የታክስ ገቢ መቀነስ፣ እና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ማነስ በኢኮኖሚው ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ሚ/ር መ/ቤቱ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጂት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው መላክቷል፡፡

አክሎም ሃገሪቷን ከዚህ ችግር ለማውጣት በሚ/ር መ/ቤቱ በኩል እየታሰበ ያለው ምንድነው ሲሉም ጥያቄ አንስተዋል፡፡

በምላሹም የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር አቶ አህመድ ሺዴ እንዳሉት በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው የሃገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ባለ ሃብቶች ግብር እንዲከፍሉ የማነቃቃት ስራ በመስራት እንዲሁም የዋጋ እድገት ጫና እንዳያመጣ ጥረት በማድረግ ብሎም የግብርና ምርቶችን በማሳደግ በተለይም የስንዴ ምርት በሃገር ውስጥ እንዲተካ በግብርናው ዘርፍ በስፋት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከቀረጥ ነጻ መብትን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ ከቀረጥ ነጻ መብት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለታለመለት አላማ እንዲያውሉ ለማድረግ የሚረዳ አጠቃላይ የፖሊሲ ማእቀፍ እያዘጋጀን ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

አያይዘውም የመንግስት የልማት ድርጂቶች የሃገር ትልቅ ሃብት እንደመሆናቸው ሃገሪቷ አሁን ካለባት የውጭ ምንዛሬ እጥረት አንጻር ለህዝብና ለመንግስት በሚጠቅም መልኩ ወደ ግል የማዞሩን ስራ በጥንቃቄ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የዋና ኦዲተር ግኝትን አስመልክቶ ባነሳው ሃሳብ የመንግስት ሃብት እየባከነና በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ተጽእኖ እየፈጠረ በመሆኑ ሚ/ር መ/ቤቱ በተሰጠው ስልጣን ልክ ግኝቶችን ባላስተካከሉ መ/ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው በአጽንኦት አስገንዝቧል፡፡

በሌላ በኩል የታክስ ስርአትን ለማሻሻል በተደረጉ ጥናቶች ለውጦች መታየት እንዳለባቸውና በሃገሪቱ ጤናማ የሆነ የገንዘብ ስርአት መኖሩ ለሃገሪቱ እድገት የራሱ ድርሻ ያለው በመሆኑ የውጭ ንግድ አፈጻጸማችንን በማሻሻል እንዲሁም የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞሩ ረገድ የነበሩ ክፍተቶችን መሙላት እንደሚገባ ጠቁመው የመንግስት መስሪያ ቤቶች የግዢ ስርአት መጓተትም በሃገሪቱ የገቢ አሰባሰብ ዝቅተኛ መሆን  ላይ  ተጽእኖ ያለው በመሆኑ በግዢ ስርአቱ የማያሰሩ እና እንቅፋት የሚሆኑትን በመለየት ምቹ የአሰራር ስርአት መዘርጋት እንደሚስፈልግ ቋሚ ኮሚቴው ሳስቧለወ፡፡