null Committee of the House hurged that tht Ethiopian Gelogical Servay Authority should solve its oudit finding facing.

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ ባለስልጣን የሂሳብ ኦዲት ግኝትን በማረምና ተገቢ የንብረት አያያዝ ስርዓትን በማሳደግ ተቋማዊ ተልዕኮውን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እንዲሰራ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበው፡፡

ከበጀት አጠቃቀም፣ ከንብረት አያያዝና አወጋገድ ጋር ያሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል በአፅንኦት እንዲሰራም ቋሚ ኮሚቴው ጠቁሟል፡፡

ሚያዚያ 30 ቀን 2011 .ም፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል ዋና ኦዲተር /ቤት በተከናወነ የሂሳብ ኦዲት መሰረት የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቨይን 2009 በጀት ዓመት የሂሳብ ኦዲት ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 2009 በጀት ዓመት የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን በማወራረድ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በተለይ ከተከፋይ ሂሳብ ጋር ሳይወራረድ የቀረ አለመኖሩ እንደ ጠንካራ ጎን የተነስቷል፤ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን በወቅቱ ሳይሰበሰብ ያልተቻለው ለምድነው የሚለውን እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ከቋሚ ኮሚቴው የተነሱ ሲሆን፤ በህግ አግባብ እና በወቅቱ ጉዳዮችን መፍታት አለመቻሉ እና ቀሪ ስራዎችም በመኖራቸው የተፈጠረ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው የማመዛዘኛ ሂሳብ መሰረት ከውጭ የገቡ ንብረቶችን የሂሳብ መዝገብ ሳይዘጋ የቆዩ ንብረቶች እንዳሉ እና ይህም በአሰራር ክፍተት የተፈጠረ ሲሆን በአሁን ላይ በርክክብ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ነው የተጠቆመው፡፡

ተቋሙ አምስት ሰራተኞች ስራ ከለቀቁ በኋላ ያልሰሩበትን ደምወዝ በድምሩ 9 ሺህ ብር በላይ ክፍያ ፈጽሞ መገኘቱ የኦዲት ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን ችግሩ ከመረጃ ፍሰት ጋር የተያያዘ እደሆነ ተነስቷል፡፡

/ቤቱ 2009 በጀት ዓመት ለየፕሮግራሞቹ የተፈቀደለት የመደበኛ በጀት ውስጥ የካፒታል በጀት ስራ ላይ ከዋለው ጋር ሲነጻጸር 10 በመቶ በላይ ከመደበኛ 12 ሚሊዮን ብር በላይ፣ ከውስጥ በጀት 29 ሚሊዮን ብር በላይና በአጠቃላይ 42 ሚሊዮን ብር አገልግሎት ላይ ሳይውል ለቀጣይ ዓመት ፈሰስ መደረጉ ለአብነት ተነስቷል፡፡ መንስኤውም ከግዢ መዘግየት ጋር በተፈጠረ ክፍተት ነው ተብሏል፤ ቋሚ ኮሚቴው የባለስልጣን /ቤቱ በመንግስት አስተዳደር ማኑዋል መሰረት ንብረት አስተዳደር ተግባራዊ መድረግ አለማድረጉን ለማጣራት ባደረገው ሂደት፤ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቋሚና አላቂ ንብረቶችን ለይቶ ከመያዝ አንፃርም ሰፊ ክፍተት አለበት ነው የተባለው፡፡