null Committee of the House visited the Jijiga branch of the Ethiopian Medical Agency.

የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ የሚታይበትን የመድሀኒት አቀማመጥ፣ አያያዝና ስርጭት ችግሮች ሊቀርፍ እንደሚገባ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ግንቦት 10 ቀን 2011 .. ቋሚ ኮሚቴው በቅርንጫፍ /ቤቱ በመገኘት የመድሀኒት አቀማመጥ፣ አያያዝና ስርጭትን ተመልክቷል፡፡

በጉብኝቱም ቅርንጫፍ /ቤቱ ክልሉን ጨምሮ ለአፋርና ለተወሰኑ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ለሚገኙ የጤና ተቋማት መድሀኒቶችን እያሰራጨ እንደሚገንኝና መድሀኒቶቹም ዘመናዊ በሆነ መንገድ እንደሚመዘገቡ በስራ ኃላፊዎቹ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የመድሀኒት መጋዘኑ ጠባብና መድሀኒቶቹን በአግባቡ ለመያዝ አመቺ አለመሆኑ እንዲሁም የመብራት እጥረት መኖሩም ነው የተጠቆመው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ቅርንጫፍ /ቤቱ ባቅራቢያው ካሉ ክሎሎች ዞኖች የጤና ተቋማት ጋር በትስስር እየሰራ መሆኑን እና ዘመናዊ የመድሀኒት ምዝገባ መኖሩን በጥንካሬ አንስቷል፡፡

በሌላ በኩል የመድሃኒት መጋዘኑ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ በጣም ጠባብና ሞቃታማ ለመድሀኒት አቀማመጥ አመቺ አለመሆኑን፣ ከመጋዘኑ ጥበት የተነሳ መድሀኒቶች በአይነታቸው በአግባቡ አለመደርደራቸውን፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ጭምር ተደባልቀው መቀመጣቸውን፣ የመብራት እጥረት መኖሩን፣ በመጋዘኑ ውስጥ የደህንነት ካሜራ (CCTV CAMERA) አለመኖሩን፣ የመድሀኒት ማጓጓዣ መኪኖችም GPS የተገጠመላቸው ያለመሆኑን በእጥረት ካስቀመጣቸው ውስጥ በዋናነት ይገኛሉ፡፡

በቀጣይ መድሀኒቶች ምቹ በሆነ ቦታ በአይነት ተለይተው ሊቀመጡ እንደሚገባና በመጋዘኑ ውስጥም የደህንነት ካሜራ አለመኖሩ ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል ለማድረግ እንቅፋት የሚፈጥር በመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ችግሮቹን መፍታት እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ / የሱፍ መሀመድ በበኩላቸው የክልሉ ቅርንጫፍ የመድሀኒት አቅርቦት መስሪያ ቤት ላይ በቋሚ ኮሚቴው በእጥረት የተነሱት ችግሮች መኖራቸውን፣ ኤጀንሲው ለግንባታ 10 ሺህ . ቦታ ቢወስድም ወደግንባታ አለመገንባቱ ጠቁመው፤ የሚመለከተው አካል ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጠውም ጠይቀዋል፡፡