null Culture, tourism and mass media affairs standing committee urged the Ethiopian broadcast authority.

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በሚሰራጩ ፕሮግራሞች ላይ የሚያደረገው የክትተልና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በባለስልጣን መ/ቤቱ በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶምና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች መስሪያ ቤቱ  ከብሮድካስት ባሻገር ፕሬስን የሚመለከቱና የማስታወቂያ ስራዎች ቁጥጥር፣ ሚዲያና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት እና ሌሎችንም ስራዎችን እንደሚያከናውን ጠቁመው፡፡

ባለስልጣኑ ከተቋቋመ በኋላ የማስፋፋት ስራ በሚመለከት አዋጁን ተከትሎ በርካታ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ቀደም ሲል በመንግስት ቁጥጥር ስር ብቻ ተወስኖ የነበረውን የብሮድካስት አገልግሎት የንግዱንም ማህበረሰብ በማሳተፍ  የተለያዩ ፈቃዶች መስጠቱንና 9 የመንግስት ሬዲዮኖችና 9 የመንግስት ቴሌቪዥኖች 10 የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም 50 የማህበረሰብ ሬዲዮ ፈቃድ መስጠቱንና 28ቱ ስራ የጀመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ዝግጀት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ 8 የሳታላይት ንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ መሰጠቱንና 6ቱ ስራ ላይ እንደሚገኙ፣ ህትመትን በተመለከተ 395 በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ ህትመቶች ምዝገባ መከናወኑን እንዲሁም ቀደም ሲል በሀገሪቱ ያልነበረ የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎት ተጀምሮ በሌሎች የማይሸፈኑ ርዕሰ ጉዳዮችን በመሸፈን ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከቋሚ ኮሚቴው የታቀደው ዕቅድ ሁሉንም አካል ያሳተፈ መሆኑ፣ የተደራጀ የስርአተ ጾታ ዘርፍ መኖሩ ከሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት የቅሬታ ሰሚ ተቋቁሞ የሰራተኛውን ቅሬታን መከታተሉ፣ አዲሱን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ፣ ህገወጥ ሚዲያዎችን ህጋዊ ለማድረግ የተደረገው ጥረት እና ተቋሙ በቋሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ግብረ መልስ ተግባራዊ ማድረጉን በጥሩ ጎን አንስቷል፡፡

በሌላ በኩል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ የተቋሙ ውጤታማነት እንዳይጎዳ የሰው ሀይል ሟሟላት፣ በሳታላይት የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በሚመለከት ባለስልጣኑ በሌሎች ተቋማት የተከተለውን አይነት ብስለትና ጥበብ የተሞላበት አካሄድ ወደ ህጋዊ መንገድ የማምጣት ስራና ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን እንድታገኝ ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

በቀጣይም ችግሮቹን ሊፈታ የሚችል የተደራጀ ጥናታዊ ስራ መስራት፣ የፖሊሲና የህግ ጉዳዮች፣ ማስታወቂያ ስራዎች ከስነምግባርና ሞራል አኳያ የሚያስተላልፉት መልዕክት ላይ ክትትል ማድረግ፣ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ፣ የአገራዊ ኮንፈረንሱን ውጤት መገምገምና ማስፋት እንዲሁም የተደራጀ የህዝብ ክንፍ እንዲኖር ማድረግ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንደሆኑ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር መስፍን ቸርነት አሳስበዋል፡፡