null Each year, seedlings transplanted are a symbol of working together and setting the boundaries between global warming and environmental degradation.

በየአመቱ የሚተከሉ ችግኞች የዓለም ሙቀትን ከመቀነስና አካባቢን ከማስዋብ ባሻገር አብሮ የመስራትና የመተባባር መገለጫ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሀምሌ 9 ቀን 2011 ዓ/ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና ሰራተኞች በየካ ክፍለ ከተማ በኮተቤና አንቆርጫ ደን ክልል 2 ሺህ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በእለቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ በርካታ የምክር ቤት አባላት በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ እንደገለጹት ዘንድሮ እንደ አገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ለመትከል በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ም/ቤቱና አካላቱ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት አቅደን ክፍለ ከተማው ለምክር ቤቱ በፈቀደለት ቦታ ላይ ችግኝ ተክለናል፤ ለተከልናቸው ችግኞችም ተገቢውን እንክብካቤ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የዕለቱ ችግኞችን የመትከል ፕሮግራምም ችግኞችን ከመትከል ባለፈ አብሮ መስራትና የመተባባር ተምሳሌት እንደሆነም ነው ያመላከቱት፡፡ ችግኞች ልክ እንደ ልጅ ተገቢውን እንክብካቤ ይሻሉ ሲሉም ምክትል አፈጉባኤዋ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ገ/እግዚአብሄር ኣርኣያ እንዳሉት የአገሪቱን የአየር ጸባይ ለማስጠበቅ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ችግኞችን ተክለናል፣ ነገር ግን የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተፈጥሮ ሀብት ልማት አጠቃቀምና ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ግዛት መኮንን በበኩላቸው ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ እንዳልሆነ እና ከችግኝ ተከላ በኋላም በርካታ የደን አያያዝ ሂደቶች እንዳሉ ገልጸው፤ ክረምት ላይ የተተከሉ ችግኞች በበጋም ሆነ በክረምት ወራቶች ተከታታይና ተገቢው ክብካቤ ሊደረግባቸው እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡