null Employees of the Secretariat of the House of Peoples’ urged to play their own role in maintaining national peace and citizens’ security

የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት  አካሄደዋል፤ ውይይቱ በምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር አባላት የተመራ ሲሆን የፅ/ቤቱ ሰራተኞች   በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛ መረጃ በመያዝና ለህብረተሰቡ በማሳወቅ ህግን በማክበርና በማስከበር ሂደት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠይቋል፤  በመጀመሪያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካጋጠሙ ችግሮች በመነሳት በአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ  አዋጅ ቆይታ  ምንም አይነት ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅቶች  ተደርገዋል ፤ ጥንቃቄዎች እየተደረጉም ነው ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የመንግስት ተጠሪ  ሚ/ር ደኤታ የተከበሩ አቶ አማኑኤል አብርሃም ተናግረዋል።

የፅ/ ቤቱ ሰራተኞች  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜያዊ መፍትሄ ለማበጀት አስፈላጊ  መሆኑን ገልፀው ፣ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች ከነባር እሴቶቻችን ያፈነገጡ አስተሳሰቦች በመሆናቸው ቦታ ሊሰጣቸው እንደማይገባና ረጅም ጊዜ የቆየውን የአብሮነት ባህላችንን ለማቆየት የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ሃላፊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል፤ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልፀዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው “የሰላም ጥቅም የሚታወቀው ሰላም ሲጠፋ መሆኑን፤ ሰላም ከሌለ  ለበርካታ አመታት የተገነቡ የልማት አውታሮች በአንድ ቀን  ሊወድሙ እንደሚችሉ  ጠቁመው’’ ሰላም ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት ፤አያይዘውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ በመረዳትና በማስረዳት፤ ተግባራዊነቱ ላይ በመደገፍና በመተባበር፤ ፀረ ሰላም ኃይሎች በሚያናፍሱት የተሳሳተ መረጃ ባለመሳብ፣ባለመነዳትና  ለተግባራቸው ባለመተባበር በማንኛውም አጋጣሚ  ሁሉ ስለ ሰላም በመስበክ  እና ለመንግስት ያለንን እምነት ማጠናከር አለብን ሲሉ አሳስበዋል  ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ፡፡