null For building strong Democratic system should ecpected to strengthening the institutions.

ለዴሞክራሲ ስረዓት ግንባታ  ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እንደሚጠበቅ ተገለጸ

በኢ.ፌ.ድ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተባባሪነት  ከግንቦት 30 እሰከ  ሰኔ 01 ቀን 2011ዓ.ም በአርባምጭ ከተማ በተካሄደው የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም ስብሰባ ላይ  ለአገራችን ዴሞክራሲ ግንብታ ጠንካራ  ተቋማት መገንባት እንሚጠይቅ ተገለጸ፡፡

በመድረኩ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ንግግር በደረጉበት ውቅት እንደ ተናገሩት የዴሞክርሲ ስረዓት ግንባታ  የፖለቲካ ቁርጠኝነት የሚጠይቅና ከዚሁ የሚመነጭ  ደግሞ ጠንካራ  ተቋማት መገንባት የሚጠይቅ ተግባር  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም የተከበሩ አፈጉባኤ  መንግስት በአሁኑ ወቅት  በዴሞክራሲ ስረዓት ግንባታ ሂደት  እያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት መጠነ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ  ያለ መሆኑን  ጠቅሰው ለአብነት ለዴሞክራሲ ስረዓት ግንብታ  እንቅፋት የሆኑ ህጎች እንዲሻሻሉ የማድረግ፡  የሚዲያ ተቋማት ስራዎቻቸውን በአግባቡ መስራት እንዲችሉ ተዘግተው የነበሩ ድህረገጾች በድጋሜ  እንዲከፈቱ መደረጋቸው ፡  በውጭ ሀገራት የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት እና  ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ  ወደ ሀገራቸው ገብተው መታገል እንዲችሉ  የማድረግ፡ ታስረው የነበሩ በርካታ ጋዜጠኞችና  የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ፡ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓረፍቲዎቹ የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም  ወደ ስራ እንዲገቡ  ተደርጓል፡፡ የአፍሪካን ቀንድ ሰላም ለማረጋገጥም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እና በጎረቤት ሀገሮች መካከል የተደረሱ መግባባቶች፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በአገሪቱ ፖለቲካ  ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት ሚናቸው መጫወት እንዲችሉ የተደረሱ መግባባቶችና ከብዙ በጥቅቱ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነጥቦች መሆናቸውነ ተጠቅሷል፡፡  አሁን ወቅት እየተደረጉ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች አገራችን ወደ ተሻለ  እድገትና ከፍታ ለማሸጋገር ተስፋ ሰጪ  እንቅስቃሴዎች  መኖሩራቸውን የሚያሳይ ነው በማለት  ገልጸዋል፡፡

የአገሪቱ ዜጎች ብሔርና ብሔረሰቦች፡  የዴሞክራሲ  ተቋማት፡የሚዲያ አካላት፡ መንግስት እና  ሁሉም ባለድረሻ አካላት በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አፈጉባኤው ጥሪያቸው አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪ ሁሉም የዴሞክራሲ ተቋማትና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በለፈው አመት በተለያዩ የስራ መስኮች ላስመዘገቡት ውጤት በማመስገን ሁሉም ተቋማት በየደረጃው እያደረጉ ያሉትን የስራ እንቅስቃሴ አጠናክረው  መቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል  የሚዲያ  አካላት በህዝብ ውስጥ የሚነሱ ጉዳዮችን ብሎም አስፈፃሚ አካላት ማድረግ ስለሚገቧቸው ጉዳዮች እንዲሁም በምክር ቤቱ መከናወን ስለሚገቡ ጉዳዮች በግልፅ ለህዝቡ  ትክክለኛና በቂ መረጃን በወቅቱ በመስጠት የተጀመረው ስራ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባት ገልጸዋል፡፡