null Honorable Ato Tagasse Chaffo received Hungarian delegations.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በሃንጋሪ ብሄራዊ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሚስተር ላስዝሎ ኮቨርትን የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በፅ/ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡
የኢትዮጵያና የሃንጋሪ ግንኙነት 40 አመታት በፊት የተመሰረተ እና ይህን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም ሀንጋሪ ... 1964 . ኢምባሲዋን በአዲስ አበባ ከፍታለች፡፡

የሃንጋሪ ፓርላማ ልዑካን ቡድንም ይህንኑ ለማጠናከር ለአምስት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው፡፡
ልዑካን ቡድኑ ከአፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ባደረገው ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት የስነ-ምጣኔ ዘርፉን ለማሳደግ እያከናወናቸው የሚገኙ በርካታ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን አድንቋል፡፡
ሃንጋሪ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጸጥታ ዘርፍና በስደተኞች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግ አፈ-ጉባኤ ሚስተር ላስዝሎ ኮቨርትን ገልፀዋል፡፡
በአገሪቱ እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የሃንጋሪ መንግስት ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም ነው አፈ- ጉባኤ ሚስተር ላስዞር አክለው የተናገሩት፡፡
አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ካጋጠማት የፖለቲካ ቀውስ ወጥታ በአሁን ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ እንደምትገኝ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀውላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ለውጥ ዘርፈ ብዙ እና መሰረተ ሰፊ መሆኑን ገልፀው፤ የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ ለማሳደግ 50 በመቶ መሆነውን የመንግስት ከፍተኛ የስልጣን ቦታ ሴቶች መያዝ መቻላቸውን ነው ለልዑካን ቡድ አባላት ያብራሩት፡፡
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከሃያ አመታት በላይ ዘልቆ የቆየውን አለመግባባት በሰላም በሁለትዮሽ ውይይት መፍታቱን እና በአሁኑ ወቅትም ሁለቱ ሃገራት በመልካም ጉርብትና እንደሚገኙ አቶ ታገሰ ገልፀዋል፡

የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና ሰላማዊ ለማድረግና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን በማጠናከር የጋራ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ነው አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የገለፁት፡፡
ኢትዮጵያ በስድተኞች ዙርያ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ለልዑካን ቡድኑ ያስገነዘቡት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፤ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች እንደምትገኝ እና የስደተኞች አዋጅ በአገሪቱ መፅደቁንም ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ  የጸጥታ ሁኔታ የተረጋጋና አስተማማኝ በመሆኑ የሃንጋሪ ባለ ሃብቶች በመምጣት በኢንቨስትመንትና በንግዱ ዘር እንዲሰማሩ ተጠይቋል፡፡
የሃንጋሪ መንግስት ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን እየሰጠ ያለውን የትምህርት እድልም አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የሃንጋሪን መንግስት አመስግነዋል፡፡