null House Speaker hands resources registration document to Commission

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሃብት ማስመዝገብና ማደስ ሰነድ ርክክብ ተፈጸመ

ፓርላማ፤ ነሐሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች ሃብት የተመዘገበበትን ሰነድ ለፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ለአቶ ፀጋ አራጌ አስረክበዋል፡፡

በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሉት ሃብትን ማስመዝገብ አገሪቷ ያላትን ውስን ሃብት በቁጠባ የመጠቀምና ልማትን የማረጋገጥ ዓላማ ያለው በመሆኑ በፌደራል ደረጃ ያሉ የመንግስት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑም በስነ-ምግባር ግንባታና በፀረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ከስነ-ምግባር ትምህርቱ ባሻገር በፌደራል ደረጃ ያሉ የመንግስት ተቋማት ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት በማጥናት የሃብት ማስመዝገብ ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አቶ ፀጋ አራጌም ሰነዱን ላስረከቡት የምክር ቤቱ አባላትና አመራሮች  ሰርተፊኬት ሰጥተዋል፡፡