null International Conference on tolerance and peace conference held.

የአለማቀፍ ፓርላማ ለመቻቻል እና ለሰላም አራተኛ ጉባኤውን በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አካሂዷል፤ ኢትዮጵያም የም/ቤቱ አባል በመሆን በተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ስምምነት ፈርማለች፡፡

ጥቅምት 17 ቀን 2012 የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የልዩ ልዩ ብሄረሰቦች መገኛና የመቻቻል ምድር ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

የአለም አገራት እርስ በርስ በቀላሉ የሚገናኙበት አጋጣሚ እየሰፋና በመምጣቱ አፀያፊ ባህሎች በቀላሉ የሚዛመቱ በመሆኑ በወጣቱ ስነ-ምግባር ዙሪያ አሁኑኑ መስራት እንደሚስፈልግ ገልፀዋል፡፡

የሰላም ጉዳይ በአንድ ድንበር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ባለመሆኑ ከአለማቀፉ ማህበረሰብ ጋር በሰላም ጉዳይ ላይ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኗን ነው የገለጹት፡፡

የአለማቀፍ ፓርላማ ለመቻቻል እና ለሰላም ም/ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አህመድ ቢን ሞሀመድ አል ጃርዋን ክብር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቬል ተሸላሚ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ 4ኛው ጉባኤ በኢትዮጵያ ማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያ በአፍሪካና በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለሰላም የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍና እውቅና ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክብር ዶ/ር አብይ አህመድና የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጉባኤው በኢትጵዮያ እንዲካሄድ በመፍቀዳቸውና ደማቅ አቀባባል በማድረጋቸውም አመስግነዋል፡፡

የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ የመቻቻልና የሰላምና አለማቀፍ የፓርላማ ህብረት ከተለያዩ አህጉሮች 60 አገራትን በአባልነት ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልፀው፤ ኢትዮጵያም የአባልነት ጥያቄ ቀርቦላት በአባልነት ተቀላቅላለች ብለዋል፡፡

የህብረቱ ዓላማውም በአለማቀፍ ደረጃ መቻቻልና ሰላም እንዲሰፍን በጋራ መስራት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በም/ቤቱ ከ40 ለሚበልጡ ለፓርላማው ህብረት አባላት የም/ቤቱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ከፍተኛ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ በዕለቱም የብሄራዊ ትያትር ቤት ባህላዊ የሙዚቃ ቡድንም አዝናኝ ዝግጅቶችንም አቅርቧል፡፡